ወቅታዊ መግለጫየምክር ቤቱን የእንባ ጠባቂና የግልግል ዳኝነት አካል ለማጠናከር የሚውል ከፈረንሳይ ኤምባሲ ጋር...

የምክር ቤቱን የእንባ ጠባቂና የግልግል ዳኝነት አካል ለማጠናከር የሚውል ከፈረንሳይ ኤምባሲ ጋር የተደረገን የድጋፍ ስምምነት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ መግለጫ

ጋዜጣዊ መግለጫ

ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት

 የምክር ቤቱን የእንባ ጠባቂና የግልግል ዳኝነት አካል ለማጠናከር የሚውል ከፈረንሳይ ኤምባሲ ጋር የተደረገን የድጋፍ ስምምነት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ መግለጫ

መገናኛ ብዙሃን ራሳቸውን በራሳቸው የሚዳኙበትን ስርዓት በመመስረት ሙያዊ ግዴታቸውን ይወጣሉ

ጥቅምት17፤2013አዲስአበባ) የኢትዮጵያ    መገናኛ    ብዙሃን   ምክር  ቤት    በሥነ   ምግባር የታነፀ  በሃላፊነት  ስሜት   ህዝብን  የሚያገለግል   ሚዲያ  በሀገራችን  እንዲጎለብት የሚሰራ  ተቋም ሲሆን  የመንግስትና  በግል መገናኛ ብዙሃንን እንዲሁም የጋዜጠኞች የሙያ  ማህበራትንና የማህበረሰብ ራዲዮን በአባልነት ያቀፈ ተቋም ነው፡፡

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሙያዊ ሀላፊነታቸውን በህግና በስነምግባር ብቻ ተመርተው እንዲያከናውኑ የሚሰራ ሲሆን  በስራ ሂደት የሚፈጠር ክፍተትን ራሳቸውን በራሳቸው የሚያርሙበት የግልግል ዳኝነት አካል አቋቁሞ ስራ ለመጀመር በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛል፤

ይህንኑ መሠረት በማድረግ ሚዲያዎች ከፍርድ ቤት በመለስ በፈቃደኝነት የሚዳኙበት ሥርዓትን ለማጠናከርና የምክር ቤቱን አባላት ጋዜጠኞች ሙያዊ ስነ ምግባር አክብረው መስራት የሚችሉበትን የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት  የሚውል የፕሮጀክት በጀት በአዲስ አበባ የሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ የብር አንድ መቶ ሺ ዩሮ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ይህ የፕሮጀክት ድጋፍ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሚስተር  ሬሚ ማሬሾ  እና በኢትዮጵያ መገናኛ    ብዙሃን   ምክር  ቤት የስራ አስፈፃሚ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ መሀከል ተፈርሟል፡፡

የበጀት ድጋፉ በምክር ቤቱ በቀረበው የፕሮጀክት እቅድ መሠረት የሚፈፀም ሲሆን በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሚስተር ሬሚ ማሬሾ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት እንደተናገሩት ሚዲያ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ መሠረት በመሆኑ መንግስታቸው ነፃና ገለልተኛ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ እንዲጠናከር ፍላጎቱ እንደሆነ ገልፀው በቀጣይነትም ከምክር ቤቱ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን  ተናግረዋል፤

የኢትዮጵያ  መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ በበኩላቸው የምክር ቤቱ የስራ ማስኬጃ በአባላት መዋጮ የሚሸፈን እንደሆነ ጠቅሰው ምክር ቤቱ ያደራጀው የእንባ ጠባቂና የግልግል ዳኝነት አካል እንዲጠናከር እንዲሁም የስነ ምግባር ደንቡን በጋዜጠኞች ውስጥ ለማስረፅ ለተቀረፀው ፕሮጀክት የፈረንሳይ ኤምባሲ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው መገናኛ ብዙሃን ራሳቸውን በራሳቸው የሚዳኙበትን ስርዓት በመመስረት ሙያዊ ግዴታቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ  መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በሚዲያ ባለሙያዎች ላይ የሚስተዋለውን የስነ ምግባር ችግሮች ለመቀነስና ራስን በራስ የመዳኘት ባህልን ለማሳደግ  በመጣር ላይ ሲሆን ፕሬስ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የማይተካ ሚና እንዳለው መሠረት በማድረግ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

የኢትዮጵያ  መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe