ወቅታዊ መግለጫከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ ‹ ጋዜጠኞች ከስራቸው ጋር...

ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ ‹ ጋዜጠኞች ከስራቸው ጋር በተያያዘ ከእስርና ክስ ከመቅረቡ በፊት ለእርስ በእርስ የቁጥጥር ስርዓት ሊቀርቡ ይገባል›

ለሁሉም ሚዲያዎች አስቸኳይ  ጋዜጣዊ መግለጫ

ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

‹ ጋዜጠኞች ከስራቸው ጋር በተያያዘ ከእስርና ክስ ከመቅረቡ በፊት ለእርስ በእርስ የቁጥጥር ስርዓት ሊቀርቡ ይገባል›

(ግንቦት 24፤2014፤አዲስ አበባ)የኢትዮጵያመገናኛ  ብዙሃን   ምክር  ቤት   በሥነ  ምግባር   የታነፀ     በሃላፊነት  ስሜት  ህዝብን  የሚያገለግል ሚዲያ  በሀገራችን  እንዲጎለብት የሚሰራ  ሲሆን ከ60 በላይ የመንግስትና  በግል መገናኛ ብዙሃንን እንዲሁም የጋዜጠኞች የሙያ ማህበራትን በአባልነት ያቀፈ ተቋም ነው፡፡

ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚሰሩ 18 ያህል ጋዜጠኞችን ህግ ከማስከበር እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር በማድረጉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ ይገኛል፤

መንግስት በቁጥጥር ስር ያረደጋቸውን ጋዜጠኞች አንዳንዶቹን ህጉ በሚፈቅደው መሠረት ፍርድ ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ የተሰጣቸው ቢሆንም አሁንም ፍርድ ቤት ያልቀረቡና የታሰሩበት ቦታ የማይታወቁ ጋዜጠኞች ስለመኖራቸው ምክር ቤቱን አሳስቦታል፡፡

በቅርቡ የፀደቀውና ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የመገናኛ ብዙኀን አዋጁም ሆነ የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ጋዜጠኞች ከስራቸው ጋር በተያያዘ  ከፍርድ ቤት መደበኛ ክስ በፊት  እንዳይታሰሩ ይከለክላል፤ ከጋዜጠኝነት ስራቸው ጋር በተያያዘ የፈጸሙት የህግ ጥሰትም ሆነ የስነ ምግባር ግድፈት ካለ በመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲውም ሆነ በአዋጁ እውቅና ለተሰጠው የእርስ በእርስ ቁጥጥር ስርዓት ተግባራዊ ማድረጊያ አማራጭ ዘዴ ሊቀርቡና ሊዳኙ ይገባል እንጂ ጋዜጠኞችን አስሮ የምርመራ ጊዜ መጠየቅ በህገ መንግስቱ እውቅና ያገኘውን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ይጋፋል ብለን እናምናለን፡፡

በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር የዋሉት ጋዜጠኞች በህግ ከተደነገገው በተቃራኒ መያዛቸው፤  በቅድመ-ፍርድ ጊዜ ለረጅም ቀናት ያለ ክስ ታስረው መቆየታቸው ፣ የታሳሪዎችን አድራሻ መደበቅ እና በቤተሰብና የህግ ባለሙያ እንድይጎበኙ መከልክል እንዲሁም መደበኛ ባልሆኑ እስር ቤቶች ማሰር የመገናኛ ብዙኀን አዋጁን የሚፃረር ተግባር በመሆኑ  ጋዜጠኞቹ የታዘሰሩት ከመገናኛ ብዙሃን ስራቸው ጋር በተያያዘ ከሆነ ክሱም ሊቀርብባቸው የሚገባው በመገናኛ ብዙሃን አዋጁ መሠረት በመሆኑ ጋዜጠኞቹ ከእስር ተለቀው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ እንጠይቃለን፡፡

ምክር ቤቱ ጋዜጠኞች በሰሯቸው ስራዎች ሀላፊነት መውሰድ እንዳለባቸውና መጠየቅ እንደሚገባቸው የሚያምን ሲሆን  ሆኖም ከህገ መንግስትቱ ጀምሮ እውቅና ያገኘው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን እንዳይጋፋ ህገና ስርዓትን በተከተለ መልኩ እንዲሆን በአፅንኦት ያሳስባል፤

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት የተላለፉ ዜናዎች፤ ፕሮግራሞችና ማስታወቂያዎች ላይ ከመንግስት ከግለሰቦችና ከተቋማት የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ተቀብሎ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወጣጥተው ባቋቋመው የግልግል ዳኝነት አካል ውሳኔ የሚያሰጥበትን ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ የጀመረ በመሆኑ መንግስትም ሆነ ሌላ አካል አቤቱታውን ከክስና እስር በፊት ለምክር ቤቱ እንዲያቀርብ በዚህ አጋጣሚ ጥሪውን ያቀርባል፤

ጋዜጠኞችን ከእስር በፊት ለምክር ቤቱ የእርስ በእርስ ቁጥጥር ስርዓት  ማቅረብ ያለመንግስት ጣልቃ ገብነት ስህተቶች እየታረሙ እንዲሄዱ እድል የሚሰጥ ሲሆን የፍርድ ቤቶችን ውድ ጊዜ እንዳይባክን ከማድረጉም በተጨማሪ ከፕሬስ ስራ ጋር ተያይዞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመንግስት የሚሰጠውን አሉታዊ ምስል ያስወግዳል ብለን እናምናለን፤

መገናኛ ብዙሃንና ጋዜጠኞች ባለፉት ጥቂት ዓመታት  ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ መምጣት ጀምሮ እስከ ህልውና ዘመቻውና ህግ የማስከበር እንቅስቃሴው ድረስ  ዘርፈ ብዙ  ተግዳሮቶችን በየተቋሞቻቸውን እያስተናገዱ እንደሆነ ምክር ቤቱ ይገነዘባል፡፡በመሆኑም  የኢትዮጵያ  መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ችግሮቹን ለመፍታት በመጣር ላይ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

የኢትዮጵያ  መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe