ዜናጋዜጠኞች ችግር መፈለግና መዘገብ ብቻ ሳይሆን ከችግር መዉጫ መንገድን የማሳየት ኃላፊነትም እንዳለባቸዉ...

ጋዜጠኞች ችግር መፈለግና መዘገብ ብቻ ሳይሆን ከችግር መዉጫ መንገድን የማሳየት ኃላፊነትም እንዳለባቸዉ ተነገረ

ጋዜጠኞች ችግር መፈለግና መዘገብ ብቻ ሳይሆን ከችግር መዉጫ መንገድ የማሳየት ኃላፊነትም እንዳለባቸዉ ሙያቸዉን የግል ጥቅም መሳሪያ በማደረግ የሙያዉ ልዕልና ማጉደፍ እንደሌለባቸው ተገለፅ፡፡

ይህ የተገለየኢትዮጲያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በፈረንሳይ ኢምባሲ ድጋፍ በሰላም ጋዜጠኝነት እና በም/ቤቱ የጋዜጠኝነት ሙያዊ የሥነ ምግባር መርህ ላይ ያተኮረ የጋዜጠኞች ሥልጠና ነሐሴ 30 እና ጳጉሜ 1 ቀን 2015 .ም በአርባምንጭ ከተማ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በዚህ ስልጠና ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ኮምኒኬሽን ትምህርት ቤት መምህር ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ “የኢትዮጲያ የሠላም ግንባታ እንቅስቃሴ እና የመገናኛ ብዙሃን ሚና ’’ በሚል ርዕስ ባቀረቡት ፅሁፍ የጋዜጠኝነት ሙያ ለአዎንታዊም ለአሉታዊም፣ ለበጎነትም ለጉዳትም ተልዕኮ ሊዉል የሚችል ባለ ሁለት ሥለት ሙያ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

trainers

ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ በኢትዮጵያ ለታየዉ ዉጊያ፣ ግጭትና የሰላም መደፍረስ መገናኛ ብዙሃን እና ጋዜጠኞች የተጫወቱትና እየተጫወቱት ያሉት ግጭት የማቀጣጠል እና የማባባስ ሚና እጅግ አስከፊ መሆኑን የተነተኑት ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች የሙያዉን መሰረታዊ መርሆች ጠብቀዉ ለህዝብ ጥቅም፣ ለሀገር ሠላም መስራት እንዳለባቸዉ አስገንዝበዋል፡፡

ጋዜጠኞች ችግር መፈለግና መዘገብ ብቻ ሳይሆን ከችግር መዉጫ መንገድ የማሳየት ኃላፊነትም አለባቸዉ የሉት ጥናት አቅራቢዉ ጋዜጠኞች ሙያቸዉን የግል ጥቅም መሳሪያ በማደረግ የሙያዉ ልዕልና እያጎደፉት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ጋዜጠኛ ያገኘዉን መረጃ ሁሉ እዉነት ስለሆነ ብቻ እንዳለ መዘገብ ሳይሆን ሊያስከትል የሚችለዉን ቀዉስ (ጉዳት) መመዘን ይኖርበታል፡፡ ጋዜጠኝነት ሙያዊ የሥነ ምግባር መርሆች ባፈነገጠ መልኩ ሀሰተኛ መረጃ እና የተዛባ መረጃ በማሰራጨት ላይ የተሰማሩ ሚዲዎችና ጋዜጠኞች ከዚህ ጥፋታቸው እንዲታረሙ አሳስበዋል፡፡

መገናኛ ብዙኃን ገለልተኛ ሆነዉ ባለመዘገባቸው የኃላ ኃላ የሚያሳፍራቸዉን ታሪክ እያስቀመጡ እንደሚሄዱ መታወቅ አለበት ብለዋል /ር አብዲሳ ዘርዓይ፡፡

በአሁኑ ሰአት በአገራችን ተጀመረዉ የሰላም ግንባታ እንቅስቃሴ በተለይም የብሄራዊ የምክክር መድረክ እና የሽግግር ፍትህ ጅማሮ ዘለቄታ ላለዉ የሰላም ማስፈን ዓላማ የሚጠቅም እንዲሆን መገናኛ ብዙሃን እና ጋዜጠኞች አዎንታዊ ሚና መጫወት እነደሚገባቸዉ ተብራርቷል፡፡

መገናኛ ብዙኃን ከመንግሥትም ሆነ ከሌሎች ኃይሎች የሚደርስባቸውን ተፅዕኖ በመታገል የሙያ ነፃነታቸዉን ማስከበር እንዳለባቸዉ የስረዱት ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ ከጦርነቱ በኃላ እንደሌሎች የጦርነቱና የግጭቱ ተዋንያን ተቋማትና አባላት ሁሉ መገናኛ ብዙሃንም መዋቅራዊ ሪፎርም እንደሚያስፈልጋቸዉ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ መገናኛ ምክር ቤት የጋዜጠኞች የሙያ ስነ ምግባር ደንብ በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለፃ ተደርጎ ዉይይት ተካሂዶበታል፡፡ በም/ቤቱ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ መሠረት አታላይ የቀረበዉ የመወያያ ፅሁፍ በስነ ምግባር ደንቡ ዉስጥ በተቀመጡ ዋና ዋና መርሆች ላይ የተኮረ ነበር ፡፡

ሙያዊ የስነምግባር መርሆች አለማቀፋዊ የጋዜጠኝነት ሙያዊ መርሆችን መሰረት አድርጎ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በሚጣጣም መልኩ የተቀረፁ መሆናቸዉንና በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ለጋዜጠኞች እንግዳ እንዳልሆኑ ተብራርቷል፡፡

Ato mesert atalay

በሙያዊ የስነምግባር ደንብ ዉስጥ ከተቀመጡት መሰረታዊ መርሆች መካከል ለመገናኛ ብዙሃንም ሆነ ለጋዜጠኞች በትግበራ እንቅስቃሴ ላይ እጅግ ፈታኝ ሊሆኑ የሚችሉ መርሆች በአቅራቢያዉ ተለይተዉ ለዉይይት የቀረቡ ሲሆን ተሳታፊዎችም ተጨማሪ ነጥቦችን በመጨመር ተወያይተዉበታል፡፡ በተለይ የገለልተኝነት፣ የሚዛናዊነትና ትክክለኝነት፣ የግጭት፣ የሃይማኖት፣ የጎሳ፣የማህበራዊ ሃላፊነት፣ የጥቅም ግጭት ፣ የጥላቻ ንግግር፣ እንዲሁም ከሙያዉ ነፃነት እና ከአገሪቱ የፕሬስ ነፃነት ጋር የተያዙ መርሆች በተግባር እንቅስቃሴ ላይ ሊገጥሙ የሚችሉ ፈታኝ ጉዳዮች መሆናቸዉ ተወስቷል፡፡

የሥነ ምግባር ደንቡ በ2015 .ም የመጀመሪያ መሻሻል የተደረገበት እና የበይነ መረብ ጋዜጠኝነት የሙያ ስነምግባርን የሚመለከቱ መርሆችን አካትቶ የተዘጋጀ መሆኑ በበጎ ጎን ተጠቅሷል፡፡ እናም የሥነ ምግባር ደንቡ የሚዲያዉንና የጋዜጠኞችን የእርስ በእርስ ቁጥጥር ሥርዓት ማራመድ የሚያስችል እንደሆነ ተሳታፊዎች ጠቅሰዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዙ ስለ ምክር ቤቱ አመሰራረት፣ አደረጃጀትና አሰራር በአቶ መሰረት አታለይ ገለፃ ተደርጓል፡፡ በዚሁ አጋጣሚ በደቡባዊ ኢትዮጵያ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትም ሆኑ የገዜጠኞች የሙያ ማህበራት የምክር ቤቱ አባል እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ለሁለት ቀናት በአርባምንጭ ከተማ በሞራ ሆቴልና ሎጅ በተካሄደዉ ሥልጠና ላይ ከጋሞ ከወላይታና ከኮንሶ አካባቢ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የተዉጣጡ ከ40 በላይ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙሃን ሃላፊዎች ተካፍለዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe