ዜናጋዜጠኞች ለአካባቢ ጥበቃ ጥረቶች መጠናከር በትኩረት ሊሰሩ ይገባል - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን...

ጋዜጠኞች ለአካባቢ ጥበቃ ጥረቶች መጠናከር በትኩረት ሊሰሩ ይገባል – የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት

የጋዜጠኝነት ሙያ ዓለምን ካጋጠማት የአካባቢ ቀውስ ለመታደግ ሚናው የጎላ መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ገለጸ።
የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ “ጋዜጠኝነት በአካባቢ ቀውስ ሁኔታ ውስጥ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።
በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት፣ በፈረንሳይ ኤምባሲ በኢትዮጵያ እና በመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በጋራ በተዘጋጀው መድረክ፥ ጋዜጠኞች በአካባቢ ጥበቃ ረገድ ያላቸውን ቁልፍ ሚና ተረድተው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ተጠይቋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ ዐሻራ እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ የመገናኛ ብዙሃን አስተዋጽኦ ጉልህ እንደነበር ተነስቷል።
መገናኛ ብዙሃኑ ይህን ገንቢ ሚናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እና ከዚህ ጎን ለጎን ለጋዜጠኞች የሚደረገው ሕጋዊ ጥበቃም እንዲጠናከር ተጠይቋል።
በኮሰን ብርሃኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe