Uncategorized‹የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀንን ስናከብር፣ ሁሉም ሰው ለመሠረታዊ ሃሳብን የመግለጽ መብት ያለውን...

‹የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀንን ስናከብር፣ ሁሉም ሰው ለመሠረታዊ ሃሳብን የመግለጽ መብት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲያድስ ጥሪዬን አቀርባለሁ።›

በየዓመቱ ሚያዝያ 25 የሚከበረውን የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ በስካይ ላይት ሆቴል  በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት፤ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንና በዩኔስኮ ትብብር በተካሄደው ዝግጅት ላይ ኢሲኤ  እና  አፍሪካ  ህብረት  ለዩኔስኮ  አገናኝ  /ቤት  ዳይሬክተርዶክተር ዩሚኮ ዮኮዘኪ   ባደረጉት ንግግር  ‹የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀንን ስናከብር፣ ሁሉም ሰው ለመሠረታዊ ሃሳብን የመግለጽ መብት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲያድስ፣ የሚዲያ ሠራተኞችን እንዲያግዝ እንዲሁም መረጃ የሕዝብ ጥቅም ሆኖ እንዲቀጥል ከጎናችን እንዲሆኑ ጥሪዬን አቀርባለሁ።› ብለዋል፡፡

ክቡር ታገሠ ጫፎ፣ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምክር ቤቱ አፈጉባኤ

የኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኤድሪስ መሐመድ

/ ትዕግስት ይልማየኢትዮጵያ መገናኛ ምክር ቤት የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ

በአካል የተገኙ እንዲሁም በይነመረብ የሚሳተፉ የመገናኛ ብዙሃን ተወካዮች

ክቡራት እና ክቡራን፣

እንደምን አደራችሁ፣ እንዲሁም መልካም የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ለሁላችን!

የዚህን በጣም አስፈላጊ ፕሮግራም አዘጋጆች በማድነቅ እንድጀምርፈቀድልኝ፡- የኢትዮጵያ ሚዲያ ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ባለሥልጣን እና ዩኔስኮ።

ይህንን ፕሮግራም ለማዘጋጀት/ለማሳካት አዘጋጆቹን ለመደገፍ የጣሩ የሚዲያ ልማት አጋሮች እንዲሁም ፍሬድሪክ ኤበርት ስቲፍቱንግ፣ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ድጋፍ (አይኤምኤስ-ፎጆ)፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ)፣ የኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ባለሙያዎች ማህበር (ኢምፓ) ጭምር ለማመስገን እፈልጋለሁ፡፡

የሚዲያ ዋና ባለድርሻ አካላት ዛሬ በኢትዮጵያ ተገኝተው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀንን ለማክበር እዚህ በመምጣታቸው ደስተኛ ነኝ። እንደሚታወቀው ዩኔስኮ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር ዓለም አቀፍ ጉባኤውን በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ከሁለት ዓመት በፊት ኢትዮጵያን መርጧል።

በዛን ጊዜ፣ የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ሃሳብን የመግለፅ እና የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን ለማሳደግ ያተኮሩ በርካታ እርምጃዎችን ወስዷል፣ ጋዜጠኞችን ከእስር ቤት መፍታት እና ድረገፆችን እና ማህበራዊ ሚዲያዎችን እገዳ ማንሳትንም ያጠቃልላል።

በመገናኛ ብዙኃን ሕጎች ላይ የሕግ ማሻሻያዎችን ጨምሮ መንግሥት ሰፊ ማሻሻያዎችን ያካሄደ ሲሆን በዚህ ዓመት አዲስ የሚዲያ ሕግምፅድቋል። 

ዩኔስኮ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት የሚያደንቅ ከመሆኑም በላይ የመረጃ ተደራሽነትን እና የኮምፒውተር ወንጀል ሕጎችን ክለሳ ጨምሮ ለተካሄዱት ማሻሻያዎች ድጋፋችንን ለማረጋገጥ እንፈልጋለን።

በዚህ ምክንያት፣ ... 2019 እና 2020 ዓ.ም ኢትዮጵያ በሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ 51 (አምሳ አንድ) እርምጃዎችን በማሻሻል በድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት መረጃ ጠቋሚ ላይ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ ጉልህ እድገት አሳይታለች፡፡ ኢትዮጵያም አምስቱቀለም ምድቦች ... 2013 ዓ.ም ጥቅም ላይ መዋል ከጀመሩ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በመረጃ ጠቋሚ ካርታ ላይ በሚገኘው የቀይ ቀለም ደረጃ መመደብ አቁማለች።

ሆኖም፣ በዚህ ዓመት ኢትዮጵያ ሁለት ነጥቦችን ዝቅ ብላለች እናም ሁሉም የሚዲያ አጋሮች፡- የሚዲያ ልማት አጋሮች፣ የመንግስት እና የብሔራዊ ሚዲያ ባለድርሻ አካላት የኢትዮጵያን የፕሬስ መረጃ ጠቋሚ የበለጠ ዝቅ እንዳይል የተቻላቸውን ሁሉ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

በሚቀጥለው ወር የኢትዮጵያ የሚዲያ ልማት ግምገማ በዩኔስኮ የሚዲያ ልማት በመጠቀም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሚዲያ ገጽታ ትንተና የሚሰጥ፣ ወሳኝ እድገቶችን የሚያሳይ እና ተጨማሪ ሥራ በሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ምክሮችን ዩኔስኮ መስጠት  ይጀምራል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም በዚህ ዓመት ከኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በይነመረብ ልማት ግምገማ ለኢትዮጵያ መጀመራችን ነው።

ውድ አጋሮች እና የተከበራችሁ ተሳታፊዎች፣

የዚህ ዓመት የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን መርህ “መረጃ ለህዝብ ጥቅም” ሲሆን መረጃን እንደ የህዝብ ጥቅም የመጠበቅ አስፈላጊነትን ለማረጋገጥ ጥሪ ሆኖ ያገለግላል።

በዓለም ዙሪያ የአገር ውስጥ የዜና ሚዲያዎች ለሚደርስባቸው የመጥፋት ስጋት አስቸኳይ ትኩረት ይፈልጋል። ይህ በመላው ዓለም በሚዲያዎች ላይ የተከሰተ ወቅታዊ ተግዳሮት ሲሆን ኢትዮጵያም ከዚህ የተለየች አይደለችም።

ቀጣይነት ባለው የለውጥ ሂደት ውስጥ የሀሰት መረጃ፣ የተሳሳተ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ተግዳሮቶችን አምጥተዋል። በዜና ሚዲያዎች የሚቀርበው የተረጋገጠ መረጃ የሀሰት መረጃን እና የጥላቻ ንግግርን ለመዋጋት ከምንጊዜም በላይ አስፈላጊነቱ ይቀጥላል።

በዚህ ትግል ውስጥ ጋዜጠኝነት ቁልፍ አካል ሆኖ ይቆያል እናም ለዚህም ነው ዛሬ ጋዜጠኝነትን እንደ ሙያ እንዲሁም ሕይወት አድን መረጃን የሚያመጡልንን ጋዜጠኞችን የምናከብረው።

ከዚህ ጋር ተያይዞ፣ እ.ኤ.አ. ግንቦት 3 ቀን 2021 ዓ.ም በሚካሄደው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን አስመልክቶ የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ከወይዘሮ ኦድሬይ አዙሌይ የተላከውን መልእክት ልግለጽላችሁ።

ከሰላሳ ዓመታት በፊት ዛሬ፣ ጋዜጠኞች፣ አዘጋጆች እና አሳታሚዎች  “ገለልተኛ እና ብዙኃን የአፍሪካዊ ፕሬስ ለማሳደግ ላይ የዊንድሆክ መግለጫ” ለፕሬስ ነፃነት ጥሪ ለማዘጋጀት ከመላው አፍሪካ ተሰባስበዋል።

ይህ ታሪካዊ መግለጫ የነፃ የመረጃ ፍሰትን ለህዝብ ጥቅም ለማድረግ ያለመ ሲሆን  ይህ ግብ ዛሬም ድረስ የሚስተጋባ ነው።

እ.ኤ.አ. ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ በተለይም በይነመረብ እና ማህበራዊ ሚዲያዎች መጀመር የተነሳ የመረጃው ገጽታ እጅግ በጣም ብዙ ለውጦችን አካሂዷል። አሁን እራሳችንን ለመግለጽ፣ መረጃ ለማግኝት እና ከሌሎች ጋር ለመገናኘት የሚያስችሉ አስገራሚ እድሎች አሉ።

ነገር ግን፣ የተሳሳቱ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮች መጨመር፣ በማደግ ላይ ያሉ የሚዲያ የንግድ ሞዴሎች እንዲሁም ስልጣን በጥቂት የግል ኩባንያዎች እጅ ውስጥ ብቻ መያዝ እያጋጠሙን ያሉ ችግሮች ናቸው።ወረርሽኙ አስተማማኝ መረጃ እንደሚያስፈልግ አመላክቷል። ለዚህም ቀውስ ትርጉም እንዲኖረን የረዳው የገለልተኛ ጋዜጠኝነት መኖር ነው።

ከፍተኛ የግል አደጋ ሊደርስባቸው ቢችልም፣ ጋዜጠኞች በቦታው ላይ በመገኘት ሪፖርት አድርገዋል፡፡ ብዙዎች በተለይ ሴቶች ዛቻ፣ እስር፣ እንግልት ደርሶባቸዋል።እ.ኤ.አ. በ 2020 ዓ.ም ስልሳ ሁለት ጋዜጠኞች ለስራቸው ሲሉ የተገደሉ ሲሆን ብዙዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸውን አጥተዋል። እኛ የምስጋና ዕዳ ለነሱ አለብን።

ወረርሽኙ እንዲሁም አሁን ያሉትን ተግዳሮቶች ይበልጥ ማባባሱን አስከትሎ ብዙ ሚዲያዎችም የገንዘብ ኪሳራ ገጥሟቸዋል።ኮሮና ቫይረስ ያስከተለው ውሸባን (የሰዎች በቤት ዉስጥ መቆየትን) ተከትሎ የበይነ መረብ አቅም የበለጠ የተጠናከረ እና አብዛኛውን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችን በበይነ መረብ የታገዙ እንዲሆኑ አስገድዷል።

እና የሐሰት መረጃ እና ወሬዎች መስፋፋት፣ የሞት እንዲሁም በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ከበድ ያሉ ውጤቶችን አስከትሏል።የዚህ ዓመት የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን መርህ፣ “መረጃ ለህዝብ ጥቅም”፣ የተረጋገጠ እና አስተማማኝ መረጃ የማያከራክር አስፈላጊነትን ያጎላል።

የተሳሳቱ መረጃዎችን እና ሌሎች ጎጂ ይዘቶችን በመከላከል የነፃ እና የባለሙያ ጋዜጠኞች መረጃን የማምረት እና ማሰራጨት ሂደት ላይ ያላቸውን ወሳኝ ሚና ትኩረት ይሰጣል። ይህ መርህ የተባበሩት መንግስታት የጋዜጠኞች ደህንነት የድርጊት መርሃ ግብር እና ያለመከሰስ ጉዳይ ጨምሮ፣ ዘላቂነት ያለው የነፃነት ደህንነትን መጠበቅ፣ የብዙሃን ጋዜጠኝነት  እና የሚዲያ ሰራተኞች ደህንነት በሁሉም ቦታ ለማረጋገጥ በዩኔስኮ የሚደረገው ጥረት ጋር ይዛመዳል።

የእነዚህ ጥረቶች አካል እንደመሆኑ መጠን፣ በይነ መረብ መድረኮች ላይ እንደ የይዘት ልከኝነት ባሉ ጉዳዮች የበለጠ ግልፅነትን ለመፍጠር፣ የሰብአዊ መብቶችን እና ዓለም አቀፍ ሀሳብን የመግለጽ ነፃነት ህጎችን በማክበር እየሰራን እንገኛለን።

ዜጎችን በሚያስፈልጋቸው የመገናኛ ብዙሃን እና የመረጃ ዕውቀት ክህሎቶች ላይ እውቀት እያስጨበጥን ይህንን አዲስ የመረጃ ገጽታ ለመዳሰስ እንዲያስችላቸው እንዲሁም በይነ መረብ ላይ ከመታለል ወይም ተጽዕኖ እንዳይደርስባቸው ለመከላከል ይችላሉ፡፡

ዛሬ፣ ግንቦት 2 እና 3 በዊንሆክ፣ ናሚቢያ በሚካሄደው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ኮንፈረንስ ላይ የዚህን አስፈላጊ ጽሑፍ 30ኛ ዓመት ክብረ በዓል ስናከብር፣ ይህ ተለዋዋጭ ገጽታ በዊንድሆክ መግለጫ ውስጥ በተሰጡት መርሆዎች ውስጥ እንዲንጸባረቅ እየሰራን ነው።

የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀንን ስናከብር፣ ሁሉም ሰው ለመሠረታዊ ሃሳብን የመግለጽ መብት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲያድስ፣ የሚዲያ ሠራተኞችን እንዲያግዝ እንዲሁም መረጃ የሕዝብ ጥቅም ሆኖ እንዲቀጥል ከጎናችን እንዲሆኑ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ክቡራት እና ክቡራን፣

በድጋሚ፣ መልካም የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን እንዲሆንላችሁ እንዲሁም ዩኔስኮ የሚዲያውን ማህበረሰብ እውቅና ለመስጠት ያወጣውን ይህንን አስፈላጊ ቀን ለማክበር ብዙ ምክንያቶችን እንድታገኙ እመኛለሁ።

አመሰግናለሁ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe