ዜናየዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን ምክንያት በማድረግ የተሰጠ መግለጫ

የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን ምክንያት በማድረግ የተሰጠ መግለጫ

ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን ምክንያት በማድረግ የተሰጠ መግለጫ

‹በኮረና ወረርሽኝና በስርጭቱ መንገዶች ዙሪያ መገናኛ ብዙሃን ከፍ ባለ የኃላፊነት ስሜት ሙያዊ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል›

(ሚያዝያ 24፤2012፤አዲስ አበባ)የኢትዮጵያመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በሥነ ምግባር የታነፀ በሃላፊነት ስሜት ህዝብን የሚያገለግል ሚዲያ በሀገራችን እንዲጎለብት የሚሰራ ሲሆን የመንግስትና በግል መገናኛ ብዙሃንን እንዲሁም የጋዜጠኞች የሙያ ማህበራትን በአባልነት ያቀፈ ተቋም ነው፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ አማካይነት በየዓመቱ ሚያዝያ 25 ወይም ሜይ 3 የሚከበረው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በዓለም ዙሪያ የህዝቦች የጤና ስጋት የሆነው የኮረና ቫይረስ በተከሰተበት ወቅት የሚከበር በመሆኑ የመገናኛ ብዙሃንና የፕሬስ ነፃነት አቀንቃኞች ዕለቱን በተለየ መልክ ይመለከቱታል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የዘንድሮውን የፕሬስ ነፃነት ቀን በተለየ ሁኔታ ለማክበር በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ደረጃ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም በወቅቱ ወረርሽን ምክንያት በታሰበው ደረጃ ለማክበር አልተቻለም፡፡

ሆኖም የሀገራችን መገናኛ ብዙሃን ወረርሽኑ ወደ ሀገራችን መግባቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረትን በመስጠት ህብረተሰቡ ለበሽታዉ ያለዉን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ ከመንግስትና ከህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ መመሪያዎችን ብሎም ዕለታዊ መረጃዎችን ለህዝቡ በማድረስ ሙያዊ ሀላፊነታቸውን ሲወጡ ቆይተዋል፡፡

በወረርሽኙና በስርጭቱ መንገዶች ዙሪያ ህብረተሰቡ ሰፊ ግንዛቤ እንዲይዝ ካልተደረገ በቀር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ምስቅልቅል ብሎም ህገ ወጥነትና የሠላም መደፍረስ የመከሰት ዕድሉ ሰፊ በመሆኑ መገናኛ ብዙሃን ከፍ ባለ የኃላፊነት ስሜት ሙያዊ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ብሎ ምክር ቤቱ ያምናል፡፡

መገናኛ ብዙሃን ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ መምጣት ጋር ተያይዞ ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶችን በየተቋሞቻቸውን እያስተናገዱ እንደሆነ ምክር ቤቱ ይገነዘባል፡፡ሆኖም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ችግሮቹን ለመፍታት በመጣር ላይ ሲሆን ፕሬስ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የማይተካ ሚና እንዳለው መሠረት በማድረግ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

በአጠቃላይ የዘንድሮው የዓለም የፕሬስ ፃነት ቀን የሚከበረው ‹ጋዜጠኝነት ያለፍርሃት ወይም ያለ አድረልዎ› /Journalism Without Fear or Favour/ በሚል መርህ ነው፤ በመሆኑም እኛም በዓሉን ስናከብር ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ መረጃ ለማግኘት ለሚሹ ወገኖች ሙያዊ ሀላፊነታችንን ያለምን ፍርሀትና አድልዎ እንደምንወጣ ተግባራዊ ምላሽ በመስጠት ሊሆን ይገባል ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት
ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

ምንጭNews.et

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe