ዜናየካናዳ ኤምሳቢ ተወካዮች ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ጋር በትብብርና በጋራ ለመስራት...

የካናዳ ኤምሳቢ ተወካዮች ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ጋር በትብብርና በጋራ ለመስራት ውይይት አካሄዱ

(መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ )የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚ  በኢትዮጵያ የካናዳ ኤንባሲ ተወካዮች ጋር መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ውይይት አካሄደ፡፡

በዚሁ ውይይት ላይ ለተወካዮቹ የምክር ቤቱ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ታምራት ሃይሉ የምክር ቤቱን አመሰራረት፣ አደረጃጀት፣ ዓላማና ግብ በተመለከተ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ምክር ቤቱ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የተለያዩ ተግባራት ማከናወኑን አስረድተዋል፡፡

በተለይ ከፈረንሳይ ኤምባሲ በተገኘ ድጋፍ በተለያዩ የሀገራችን ክልሎች ለሚገኙ ጋዜጠኞች ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከመጡ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር በምርጫ ስነምግባር ደንብና በጋዜጠኝነት የስነምግባር መመሪያ ላይ ስልጠና የተሰጠ ከመሆኑም በላይ በሰላም ጋዜጠኝነትና ግጭት አወጋገድ ዘገባም ስልጠና መሰጠቱን አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በአሁኑ ወቅት ትኩረት ሰጥ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

ምክትል ስራ አስፈፃሚው ምክር ቤቱ ሲቋቋም በ19 አባላት መሆኑን አስታውሰው በአሁኑ ወቅት 60 ተቋማት የምክር ቤቱ አባል ሆነዋል ብለዋል፡፡ ምክር ቤቱ በዩኔስኮ ድጋፍ የአምስት ዓመት ስራቴጂክ ፕላን አሰርቶ ተግባራዊ እያደረገ ሲሆን በተለይ የምክር ቤቱን ገለልተኛ የግልግል ዳኝነት አካል ማቋቋም ጊዜ የወሰደ ተግባር ከባድ እንደነበሩ ለተወካዮች አስረድተዋል፡፡

የቤቱ ስራ አስፈፃሚ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ በበኩላቸው እንደገለፁት የምክር ቤቱ ዋነኛ የህዝብ አግልገሎት ተጋባሩን ለመወጣት የግልግል ዳኝነት አካልን በማቋቋም ስራ ለመጀመር በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው የተቋቋመው የግልግል ዳኝነት አካል ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጣ መሆኑንና በፈቃደኝነት የሚያገለግሉ መሆናቸው አስረድተዋል፡፡

እንዲሁም ምክር ቤቱ ሚዲያውን በተመለከቱ የሚወጡ ህጎች ላይ ከሚመለከታቸው የተለያዩ የመንግስት ሃላፊዎች ጋር ውይይት ያካሄደ መሆኑን ሰብሳቢው ገልፀው ምክር ቤቱም የአፍሪካ ሚዲያ ካውንስል አባል ለማድረግ እየጣርን እንገኛለን ብለዋል፡፡

የምክር ቤቱ የጠቅላላ ጉባዔ ሰብሳቢ ወ/ሮ ትዕግስት ይልማእንደገለፁ በአጠቃላይ ያለፉት ዓመታት የተለያዩ ችግሮች ነበሩ፡፡ በተለይ በሀገራችን በተከሰተው ኮቪድ፣ ምርጫ፣ ጦርነት እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ካውንስሉ በተቻለ መጠን ስራውን ለማከናወን ተንቀሳቅሶ የተለያዩ ተግባራትን አከናውነናል ብለዋል፡፡ ሆኖም  ኮቪድ 19 ባስከተለው ወረርሽኝ ምክንያት ሚዲያዎች ላይ በፋይናንስም ሆነ በሰው ላይ ጉዳት መድረሱን አስረድተዋል፡፡

በመጨረሻም ከተወካዮቹ የቀረቡ ጥያቄዎች በስራ አስፈፃሚ አባላት መልስ የተሰጠ ሲሆን በኢትዮጵያ የካናዳ ኤንባሲ ተወካይ ማዳም ባርባራ ሐርቬይ በሰጡት አስተያየት የተደረገላቸው ገለፃ እንደተደሰቱና ስለምክር ቤቱ አሰራር ማወቃቸውን ገልፀው በተቻለ መጠን የአጭር እና የረጅም ጊዜ ፕሮጀክቶች ተቀርፆ በትብብር ከምክር ቤቱ ጋር እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

Ms Barbara Harvey
Ms Barbara Harvey

በመቀጠልም በዩኔስኮ የመገናኛ እና የመረጃ ዘርፍ የፕሮግራም ኦፊሰር  የሆኑት አቶ አደራው ገነቱ እንደገለፁት ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ጋር ድርጅታቸው የቆየ ግንኙነት እንደነበረው እና በተለይ የኢትዮጵያ የሚዲያ ዘርፍ ጥምረት በመመስረት ከምክር ቤቱ ጋር ለመካከለኛ ጋዜጠኞች በስራ ላይ ላሉ ጋዜጠኞች የስልጠና ካሪኩለም ቀረፃ ማድረጉንና የአለም የፕሬስ ቀንም በትብብር ከምክር ቤቱ ጋር በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲከበር ማድረጉን አስረድተዋል እንዲሁም ምክር ቤቱ ከአቻ ድርጅቶች ጋር በተለይ ከኬኒያ ሚዲያ ካውንስል የልምድ ልውውጥ እንዲያደርግ ድጋፍ አድርጓል ብለዋል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe