Uncategorizedየኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጋር ውይይት አደረገ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጋር ውይይት አደረገ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጋር በጋዜጠኞች አቅም ግንባታ፣ ሙያዊ ስነ-ምግባር እንዲሁም በሚዲያ አጠቃቀም ላይ ህብረተሰቡን የማንቃት ስራዎችን በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ምክር ቤቱ የጋዜጠኝነት ሙያዊ መርሆዎችን ያከበረ እና ለብሔራዊ ጥቅም የቆመ የመገናኛ ብዙኃን እንዲፈጠር ትኩረት አድርጎ መስራት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን ለዚህም ባለሥልጣኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ በበኩላቸው ምክር ቤቱ እያከናወናቸው ያሉትን የአቅም ግንባታ ስራዎች በማጠናከር የመገናኛ ብዙኃን ኢንዱስትሪው በሚያጋጥሙት ችግሮች ዙሪያ ከባለሥልጣኑ ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ የባለሥልጣኑ ኃላፊዎችና የም/ቤቱ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ባለሥልጣኑ ከዚህ በፊት ከምክር ቤቱ ጋር የመግባቢያ ስምምነት በተፈራረመው መሠረት የተለያዩ ስራዎችን በጋራ እየሰራ ይገኛል፡፡

ምንጭEMA

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe