ዜናየኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የሚዲያ ስነ-ምግባር በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ያስጠናውን የዳሰሳ...

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የሚዲያ ስነ-ምግባር በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ያስጠናውን የዳሰሳ ጥናት ይፋ አደረገ

የሚዲያ ስነ-ምግባር በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ የተጠና የዳሰሳ ጥናት ይፋ ሆነ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የሚዲያ ስነ-ምግባር በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ያስጠናውን የዳሰሳ ጥናት ይፋ አደረገ።
ምክር ቤቱ ለሁለት ወራት የሚዲያ ስነ-ምግባር በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ የስጠናውን የዳሰሳ ጥናት ዛሬ ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ በወቅቱ እንደገለጹት፤ የሚዲያ ነጻነት ለድርድር የሚቀርብ አጀንዳ ባይሆንም በስነ-ምግባር የታነጸ ሚዲያ መገንባት አስፈላጊ ነው።

በሐይማኖትና በብሔር ሀሰተኛና የጥላቻ ንግግር በገፍ እየተሰራጨ ነው ያሉት አቶ አማረ፤በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን የስነ-ምግባር ጉድለት ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ይገኛልም ብለዋል።

Particpant
እንደ አቶ አማረ ገለጻ፤ የሀገሪቱ የሰላም ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ከገባበት ጉዳዮች አንዱ የሚዲያ ስነ-ምግባር ጉድለት ነው።
በኢትዮጵያ አብዛኛው የሚዲያ ስነ-ምግባር ተፈጻሚ እየሆነ አለመሆኑ በጥናቱ ተመላክቷል።
በቂ ስልጠና አለማግኘት፣ አብዛኛው ሰራተኛ ጋዜጠኛ አለመሆኑ፣የተለያዩ አካላት ጣልቃ ገብነት፣ የማህበረሰቡ ለሚዲያ ያለው የግንዛቤ እጥረት፣ በሚዲያ ዘርፍ የተቋቋሙ ተቋማት በትብብር አለመስራት፣ ለሚዲያ ስነ-ምግባር መጣስ ዋና ዋና ምክንያት መሆኑን በጥናቱ ተረጋግጧል።
የአርታኢያን መድረክ ማጠናከር፣ በጋራ መስራት፣ የሚዲያ ነጻነት ማረጋገጥ፣ ዓመታዊ መድረኮች እንዲጠናከሩ ማድረግ፣ ዓመታዊ ዎርክ ሾፕ ቢለመድና የመሳሰሉት ለሚዲያ ስነ ምግባር ጥሰት ለመቀነስ እንደሚረዳ ተገልጿል።
በዳሰሳ ጥናቱ ሰባት በሚዲያ ዘርፍ የተቋቋሙ ተቋማት የተሳተፉ ሲሆን፤ ጥናቱ በገለልተኛ አካል ተጠንቷል።
በዳሰሳ ጥናቱ የተሳተፉት አካላተ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤትነ ጨምሮ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤የኢትዮጰያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን፤የኢትዮጵጵያ መገናኛ ብዙሃን ሴቶች ማህበር፤መርሳ ሚዲያ ኢንስቲቲዩት፤ የኢትዮጵያ አርትያን ማህበርና አይኤምኤስ በጥናቱ ዙሪያ ወይይት አድርገዋል፤
ምንጭ(ኢ ፕ ድ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe