ዜናየኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ስለ ጋዜጠኞች እስራት

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ስለ ጋዜጠኞች እስራት

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ስለ ጋዜጠኞች እስራት

(ዶይቸ ቬለን ይቃኙ)የጋዜጠኞች በጅምላ መታሰር በቅርቡ ተበራክቷል። ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ብቻ ከ18 ያላነሱ ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገዋል። ከታሰሩት ጋዜጠኞች መካከል አንዳንዶቹ ፍርድ ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ የተሰጣቸው ቢሆንም፤ አሁንም ፍርድ ቤት ያልቀረቡና የታሰሩበት ቦታ የማይታወቁ ጋዜጠኞች መኖራቸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ያሳስበናል ብሏል።

የጋዜጠኞች በጅምላ መታሰር በቅርቡ ተበራክቷል። ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ብቻ ከ18 ያላነሱ ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገዋል። ከታሰሩት ጋዜጠኞች መካከል አንዳንዶቹ ፍርድ ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ የተሰጣቸው ቢሆንም፤ አሁንም ፍርድ ቤት ያልቀረቡና የታሰሩበት ቦታ የማይታወቁ ጋዜጠኞች መኖራቸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ያሳስበናል ብሏል። ጋዜጠኞች  ከሕግ ውጭ  ከመያዛቸው ባሻገር  ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ክስ ሳይመሰረትባቸ ታስረው መቆየታቸው፣ ያሉበትን መደበቅ እና በቤተሰብና የሕግ ባለሞያ እንዳያገኙ መከልክል የመገናኛ ብዙኀን አዋጁን የሚፃረር ተግባር ነውም ብሎዋል።

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት እየተበራከተ የመጣው የጋዜጠኞች እስራት እና እንግልት አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ረቡዕ ግንቦት 24 ቀን፣ መግለጫ አውጥተዋል። በኢትዮጵያ እስካሁን 18 ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገዋል። መንግስት በቁጥጥር ስር ያረደጋቸው ጋዜጠኞች አንዳንዶቹ  ፍርድ ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ የተሰጣቸው ቢሆንም አሁንም ፍርድ ቤት ያልቀረቡና የታሰሩበት ቦታ የማይታወቁ ጋዜጠኞች ስለመኖራቸው ምክር ቤቱን አሳስቦታል ብለዋል ጋዜጠኞች  ከሕግ ውጭ  ከመያዛቸው፤ ባሻገር  ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ክስ ሳይመሰረትባቸ ታስረው መቆየታቸው፣ ያሉበትን መደበቅ እና በቤተሰብና የሕግ ባለሞያ እንዳያገኙ  መከልክል የመገናኛ ብዙኀን አዋጁን የሚፃረር ተግባር ነው ተብሎዋል።  ጋዜጠኞቹ የታሰሩት ከመገናኛ ብዙኃን ሥራቸው ጋር በተያያዘ ከሆነ ክሱም ሊቀርብባቸው የሚገባው በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ መሠረት መሆን ይኖርበታል ብለዋል አቶ ታምራት ኃይሉ። የኢትዪጵያ መገናኛ  ብዙኃን ሥራ አስፈፃሚ በየግዜው የሚታየው የጋዜጠኞች እስራት እና እንግልት የሕግ ከለላ አለማግኘት በሀገራችን ሀሳብን በነፃነት የመገፅ መብትን ጥያቂ ውስጥ ከመክተቱም ባሻገር  በሞያው ላይ ያሳደረውን ተፀኖ ክረፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ሐና ደምሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ

https://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%88%98%E1%8C%88%E1%8A%93%E1%8A%9B-%E1%89%A5%E1%8B%99%E1%8A%83%E1%8A%95-%E1%88%9D%E1%8A%AD%E1%88%AD-%E1%89%A4%E1%89%B5-%E1%88%B5%E1%88%88-%E1%8C%8B%E1%8B%9C%E1%8C%A0%E1%8A%9E%E1%89%BD-%E1%8A%A5%E1%88%B5%E1%88%AB%E1%89%B5/a-62011896?maca=amh-Facebook-dw&fbclid=IwAR2_erfKxAdnjRjEjqeSUAK2ue8pOZv3wHgEVs3nedkccl8vJwBqB_bg5gQ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe