ዜናየኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

 የህትመትና ሳተላይት ክፍያ በመጨመሩ ምክንያት መገናኛ ብዙኃን የመዘጋት ዕጣ እየገጠማቸው መሆኑን የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
ምክር ቤቱ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ እያካሄደ ሲሆን በመክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ግዛው ተስፋዬ መገናኛ ብዙኃን በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ውስጥ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ ትዕግስት ይልማ መገናኛ ብዙኃን በፀጥታ ምክንያት ለገጠማቸው የፋይናንስ ችግር መንግስት ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል። ምክር ቤቱ በፋይናንስና በፀጥታ ችግር ምክንያት በሚፈለገው ልክ ስራውን በአግባቡ ማከናወን አለመቻሉንም አመልክቷል። መንግስት ለሃገር እድገት የመገናኛ ብዙኀኑን አዎንታዊ ሚና ተረድቶ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥም ተጠይቀዋል።
የምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ ትዕግስት ይልማ፤ ምክር ቤቱ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ስራዎችን ሰርቷል ብለዋል። በዚህም ዘርፉ ለሃገር እድገት ያለውን ሚና የተሻለ ለማድረግ ዕድል መፈጠሩን ጨምረው ጠቁመዋል።
ምክር ቤቱ በዓመታዊ ጉባኤው ሪፖርት ማቅረብ፣ የግልግል ዳኝነት ሪፖርት ማድመጥ፣ ዓመታዊ ኦዲት እና የ2016 ዓመታዊ እቅድ ማቅረብ ጨምሮ የተወሰኑ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀፆችን ማሻሻል እንዲሁም በተጓደሉ የምክር ቤቱ አመራር አባላት ምርጫ አካሂዳል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት የስራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ የምክር ቤቱን የሁለት አመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፤
በዚህም መሰረት በተጓደሉ የምክር ቤቱ የጠቅላላ ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢና ጸሃፊ ቦታ ከኦሮሚያ ጋዜጠኞች ማህበርና ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን ማህበር አመራሮች ተመርጠዋል፤
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ ከምስረታው ጀምሮ አስተዋጽኦ ላደረጉ የቀድሞ አመራሮችና ተቀማት የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቸዋል፤
በ2011 ዓ.ም በተሻሻለው የሲቪክ ማህበራት አዋጅ መሠረት ሰኔ 7/2011 ዓ.ም ምክር ቤቱ በሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ኤጄንሲ ሕጋዊ ፈቃድ አግኝቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe