Uncategorizedየኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ጠንካራ ባለሙያዎች እንዲፈጠሩ ለጋዜጠኞች በሚሰጠው ስልጠና...

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ጠንካራ ባለሙያዎች እንዲፈጠሩ ለጋዜጠኞች በሚሰጠው ስልጠና ድጋፍ እንደምታደርግ ፈረንሳይ አስታወቀች

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን አያካሄደ።የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ ኢድሪስ በዚህ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ለአገር ሁለንተናዊ እድገት የመገናኛ ብዙሃን ሚና ከፍተኛ ከፍተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ለአገር ሁለንተናዊ እድገት የመገናኛ ብዙሃን ሚና ህዝብን በማንቃት ሚናቸው ከፍተኛ ነው። ጠንካራና ሚናውን በአግባቡ የሚወጣ መገናኛ ብዙሃን ሲኖር ሚናውን በአግባቡ የሚወጣ ህዝብና መንግስት ይኖራል ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ መገናኛ ብዙሃን የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ህዝብን በማንቃት፣ ምርጫ 2014 በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል።

Participants
Participants
በተለይም በአገር ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ የውጭ ጫናን በማጋለጥ ሰፊ ስራ መስራታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኢምባሲ ምክትል ዳይሬክተር ሚስተር ካሉድ በሊቪን ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት ፈረንሳይ በኢትዮጵያ ነጻ የሆነ መገናኛ ብዙሃን እንዲኖር እግዛ እያደረገች ነው።
በብዙ ጉዳዮች ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ጋር የተለየ ግንኙነት ያላት ሲሆን ጠንካራ ባለሙያዎች እንዲፈጠሩ ምክር ቤቱ ለጋዜጠኞች በሚሰጠው ስልጠና ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።
በጠቅላላ ጉባኤው የምክር ቤቱ የሁለት አመት አመታዊ የስራ አፈጻጸም፣ የአመቱ የኦዲት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን የ2014 እቅድና አዳዲስ አባላትን በማስተዋወቅ ፍጻሜውን ያገኛል ተብሏል።
በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኢምባሲ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ተወካይ፣ የመገናኛ ብዙሃን ሃላፊዎች፣ የጋዜጠኝነት መምህራንና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ምንጭ(ኢ.ፕ.ድ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe