ዜናየኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ከባንግዳለዴሽ አምባሳደር ጋር ውይይት አካሄደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ከባንግዳለዴሽ አምባሳደር ጋር ውይይት አካሄደ

በኢትዮጵያ የባግላዴሽ አምባሳደር የሆኑት ሚስተር ሚድ ናዙርል ኢስላም ከኢትዮጵያ መገናና ብዙሃን ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በምከር ቤቱ ጽ/ቤት ውይይት አካሂደዋል፤

በኢትዮጵያ የባንግዳለዴሽ አምባሳደር ሚስትር ሚድ ናዙርል የምክር ቤቱን ጽ/ቤት በጎበኙበት ወቅት እንደተናገሩት ኢትዮጵያና ባንግላዴሽ ታሪካዊ ግንኑነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸው በመጥቀስ ባንግደላዴሽ በሚዲያው ዘርፍ ከኢትዮጵ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ጋር ተባብሮ የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፤

በባግደላዴሽ በርካታ የመንግስትና የግል መገናኛ ብዙሃን እንዳሉ የጠቀሱት አምባሳደሩ ጋዜጠኞች ሙያቸውን ለማሳደግ የሚገናኙበትና ስራቸውን የሚያሳድጉበት የሚዲያ ካውንስ እንዳለ በመጥቀስ በአቅም ግንባታና በስልጠና ዘርፍ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፤

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤተ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ ወ/ሮ ትዕግስት ይልማ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ባንግዳለዴሽ በዩ ልዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በኢትዮጵያ እንደምትሳተፈው ሁሉ በሚዲያው ዘርፍ አብሮ ለመስራት ማቀዷ የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት የበለጠ የእንደሚያሳድገው ገልጸዋል፤

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክረ ቤት የስራ አስፈፃሚ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ በበኩላቸው አምባሳደሩ የምክር ቤቱን ጽ/ቤት ለመጎብኘት መምጣታቸውን አመስግነው ባንግላዴሽ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ ግንኙነት ከምክር ቤቱ ጋር ባደረጉት ውይይት የበለጠ  ማሳደግ እንደሚቻል በመግለፅ የበለጠ መቀራረብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፤

EtMc with Bangladesh Ambassdor
EtMc with Bangladesh Ambassdor

የምክር ቤቱን ያለፉት ዓመታት እንቅስቃሴ ያብራሩት የምክር ቤቱ ስራ አስፈፃሚ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ታምራት ኃይሉ ምክር ቤቱ ባለፉት ዓመታት የጋዜጠኞችን አቅም ለመገንባት በርካታ ስልጠናዎችን በአዲስ አበባ በክልሎች መስጠቱንና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መጓዙን አብራርተዋል፤ የምክር ቤቱ ዋና ተግባር የሆነውን የግልግል ዳኝነት አካል ተደራጅቶ ስራ መጀመሩንና አቤቱታዎችም መቀበል መጀመሩንም አክለዋል፤

አምባሳደር ሚድ ከመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤቱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠንከር በተለይም  በስፖርትና በቱሪዝም ዘርፍ ካሉ ጋዜጠኞች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የሁለቱን ሀገሮች ልምድ ልውውጥ የማሳደግ እቅድ መኖሩን ተናግረዋል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe