የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ምክር ቤት ከሀረሪ ብዙሀንመ መገናኛ ኤጀንሲ እና ከድሬደዋ እና ለተወጣጡ ጋዜጠኞች በሰላም ጋዜጠኝነት ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና ነሃሴ 18 ቀን 2015 ሰጥቷል።
ስልጠናው በዋናነትም በሰላም ጋዜጠኝነት; የጥላቻ ንግግር እና በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ምክር ቤት አሰራር ዙሪያ ያተኮረ ነበር።
ለተሳታፊ ጋዜጠኞች ስልጠና የሰጡት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ መምህር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ እንደገለፁት የሚዲያ ባለሞያዎች ምን ጊዜም ለህዝብ አስፈላጊ መረጃዎችን መግለፅ እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ሀገራዊ ሁኔታዎችን በመረዳትና በተለይም ሀገራዊ ሰላምን ምንግዜም የፀና ለማድረግ የሚደያ ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
በሰላም ጋዜጠኝነትና በሌሎች የስልጠናው ርዕሰ ጉዳዮችም ለጋዜጠኞች ገለፃ ሰተዋል።
በስልጠናው የተካፈሉ ጋዜጠኝች በበኩላቸው የሰላም ጋዜጠኝነት መርህን በሚገባ ለመተግበር ጠቃሚ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
የኢትዮጲያ መገናኛ ብዙሀን ምክር ቤት የሚዲያ ነፃነትን ማስጠበቅ ; ሙያዊ ብቃትን ማጎልበት እና የሚዲያ አለመግባባቶችን መፍታት ራዕይ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተገልጿል።