ዜናየሶማሌ ክልል ጋዜጠኞች ማህበር ተመሰረተ

የሶማሌ ክልል ጋዜጠኞች ማህበር ተመሰረተ

በክልሉ የሚገኙ ጋዜጠኞችን በማቀፍ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ዘገባ ለህብረተሰቡ የማቅረብ ከአላማዎቹ መሀከል ያደረገው የሶማሌ ክልል ጋዜጠኞች ማህበር መስከረም፣ 9 ቀን 2014 ዓ.ም በጂግጂጋ ተመሰረተ፤
በዚሁ የምስረታ በአል ላይ የተገኙት የክልሉ የመንግሥት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሊ በደል እንደተናገሩት ከለውጡ በፊት የክልሉ ጋዜጠኞች በሙያቸው እንዳይሰሩ የነበረው አስተዳደር እንቅፋት እንደነበር ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት ግን የሚዲያ ባለሙያዎች በነፃነት የሚሰሩበት ሁኔታ መፈጠሩን አስረድተዋል።
ጋዜጠኞች ከረብሻና ግጭት ቀስቃሽነት ርቀው ሚዛናዊ ዘገባ የሚያቀርቡ ከሆነ ክልሉ ተጠቃሚ የሚሆን በመሆኑ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ያሉት አቶ አሊ ዘር ፤ቋንቋና ሀይማኖት ሳትለዩ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ጋዜጠኞችን በሙሉ በአባልነት ልታቅፉ ይገባል ብለዋል።

Ato Tamerat Hailu
Ato Tamerat Hailu

በእለቱ በማህበሩ የምስረታ በአል ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ታምራት ኃይሉ በበኩላቸው እንደተናገሩት እስከ አሁን ድረስ የክልሉ ጋዜጠኞች መብታቸውንና የሙያ ነጻነታቸውን ለማስከበር አለመደራጀታቸው ትልቅ ክፍተት እንደነበር ጠቅሰው ለበጎ ነገር ምንግዜም ረፈደ አይባልምና አሁን ማህበሩ መመስረቱ ሙያውን ይበልጥ ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል።

ምክር ቤቱ አንጋፋውን የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበርን ጨምሮ የአማራ ጋዜጠኞች ማህበር፤ የኦሮሚያ ጋዜጠኞች ማህበር፤የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር፤ የመገናኛ ብዙሃን ሴቶች ማህበር፤ የቱሪዝምና ባህል ጋዜጠኞች ማህበርና፤ ዋቢ የግል ፕሬስ አሳታሚዎች ማህበር፤የብሮድካስተሮች ማህበር፤ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማሀበር፤ እንዲሁም የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን ማህበርና ከ50 በላይ የሚሆኑ የሚዲያ ተቋማትን በአባልነት ይዞ  የጋዜጠኝነት ስነ ምግባርን ለማስጠበቅ ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ታምራት የሱማሌ ክልል የጋዜጠኞች ማህበርም የምክር ቤቱ አባል በመሆን የሙያ ስነምግባር የማስጠበቅ እንቅስቃሴውን እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዋል።

ማህበሩ በአጭር ጊዜ ጠቅላላ ጉባዔ በመጥራት አመራሮችን እንደሚመርጥ ተገልጾአል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe