ዜናየሐሰተኛ ዜና ስርጭትን ለማስቀረት ተቋማት ተገቢውን መረጃ ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለጸ

የሐሰተኛ ዜና ስርጭትን ለማስቀረት ተቋማት ተገቢውን መረጃ ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለጸ

የሐሰተኛ ዜና ስርጭትን ለመቆጣጠር የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት ለመገናኛ ብዙኃን ተገቢውን መረጃ ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለጸ።

በዓለም ለ30ኛ በኢትዮጵያ ለ7ኛ ጊዜ የተከበረው የፕሬስ ቀን ትናንት በአዲስ አበባ ሲከበር የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ባቀረቡት የመነሻ ጽሑፍ መነሻነት በተደረገው ውይይት፤ የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት ለመገናኛ ብዙኃን ተገቢውን መረጃ ሊሰጡ እንደሚገባ ተገልጿል።

የቁም ነገር መጽሔት ዋና አዘጋጅ አቶ ታምራት ኃይሉ ባቀረቡት የውይይት መነሻ ጽሑፍ እንዳቀረቡት እየተስፋፋ የመጣው የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት አገሪቱን እየጎዳ ይገኛል። ይህ የሚሆነው ደግሞ ዋናዎቹ መገናኛ ብዙኃን ከመንግሥትም ሆነ ከግል ተቋማት ቀድመው መረጃ ለማግኘት ስለሚቸገሩ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሐሰት መረጃዎችን እያሰራጩ በመሆኑ ነው። አንዳንድ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አፋቸውን ሞልተው መረጃ የሚከለክሉ ቢሆንም ተጠያቂ ሲሆኑ ግን አይታዩም።

በመሆኑም ‹‹የመንግሥት አመራሮች ለአፈጻጸማቸው ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው በመጥቀስ በህግ መሰረት እንኳን ጋዜጠኞች የትኛውም ግለሰብ የጠየቀውን መረጃ የማግኘት መብት እንዳለውም አብራርተዋል። በተጨማሪ በመንግሥት ኃላፊዎች ሳይቀር ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች እየተደረጉ ይገኛል። ያሉት አቶ ታምራት መረጃ መስጠት ግጭትን ይቀሰቅሳል ብሎ ከመፍራት ይልቅ በኃላፊነት ላይ ትክክለኛ መረጃ የሚሰጥ ሰው መቀመጥ እንደሚኖርበት ተናግረዋል።

«በኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካና ጋዜጠኝነት ተደበላልቋል፤ የመገናኛ ብዙኃን ታዳሚውም ፖለቲከኛና ጋዜጠኛው ተምታቶበታል» ያሉት ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ሙላቱ አለማየሁ ናቸው።

አንደ ዶክተር ሙላቱ ማብራሪያ በኢትዮጵያ ፖለቲከኛና ጋዜጠኝነት በመደበላለቁ መረጃ የሚሰጡ ምንጮች ሲያመጡ ከየራሳቸው ፍላጎት አንፃር ነው፤ መረጃውን የሚያስተላልፉበት መንገድም ከራሳቸው ፖለቲካዊ ፍላጎት የመነጨ ሆኖ ይታያል። የሐሰተኛ መረጃዎች ስርጭትም ሌላው የዘመኑ ችግር ሆኗል። መገናኛ ብዙኃን መፎካከር ያለባቸው ቀድሞ በማሰራጨት ሳይሆን፤ ጥራት ያለውና ትክክለኛ መረጃ ለህዝብ በማድረስ ሊሆን ይገባል ብለዋል። በመረጃ ጥራት ላይ መገናኛ ብዙኃን የልምድ ልውውጥ ማድረግ እንዳለባቸው በመጠቆምም፤ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍሎች ከመገናኛ ብዙኃን ጋር በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ዶክተር ሙላቱ አሳስበዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe