ወቅታዊ መግለጫኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ሚዲያ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ለመከላከል የቀረቡ ስልታዊ መፍትሔዎች

ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ሚዲያ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ለመከላከል የቀረቡ ስልታዊ መፍትሔዎች

ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ሚዲያ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ለመከላከል የቀረቡ ስልታዊ መፍትሔዎች

 መግቢያ፦ የሚዲያ ስራ በቋፍ ላይ

ሚያዝያ 28 ቀን 2012 ዓ.ም COVID-19 በመገናኛ ብዙሃን ስራ ላይ ስላለው ተፅእኖ ለመወያየት የኢትዮጵያ ሚዲያ ባለድርሻ አካላት የቪዲዮ ውይይት ጠሩ። አጀንዳቸው በሰዎች ጤና ላይ በአለም ዙሪያ ቅስፈታዊ አደጋ እየፈጠረ ያለው የኮሮና ቫይረስ ወርርሽ የሚዲያ ተቋሞችን ሕልውና ፈጽሞ ሳያጠፋው፤ በጋራ መፍትሔ እንፈልግ የሚል ነበር።  በውይይቱ ላይ የህዝብና የንግድ መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም የማህበረሰብ ሚዲያዎች ፣ የጋዜጠኞች ማህበራት ፣ የመንግስት ተወካዮች ፣ ተደማጭነት ያላቸው አርታኢዎች ፣ ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ልማት ቡድኖች (መርሳ ሚዲያ)የተሳተፉ ሲሆን፤ ተሳታፊዎቹ የሚዲያ ኢንዱስትሪውን ፈታኝ ሁኔታዎች ለይተው በመወያየት በጋራ መፍትሔዎችን ለማፈላለግ ቃል ገብተዋል ፡፡

የመገናኛ ብዙሃኑ በኮቪድ-19 ምክንያት ከፍተኛ የማስታወቂያ ገቢ ማጣታቸውና ተቋማቱ የዕለት ዕለት ስራቸውን ሳያስተጓጉሉ ለማከናወን የጋዜጠኞቻቸውን ደህንነት ማስጠበቅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ለተጨማሪ ወጪ መዳረጋቸውን ገለጹ።  የማስታወቂያ ገቢ ላይ የታየው ማሽቆልቆል ለረጂም ጊዜ በስራው ላይ የቆዩ የሚዲያ ተቋማት ላይ ከ60% በላይ መሆኑ በውይይቱ ተምልክቷል።[1] የህዝብ መገናኛ ብዙሃኑም እንድ ንግድ መገናኛ ብዙሃን ሁሉ ከፍ ያለ የማስታወቂያ ገቢ የማሽቆልቆል ችግር አጋጥሟቸዋል፡፡ የሀገሪቱ ትልቁ የህዝብ መገናኛ ብዙሃን የሆነው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኮቪድ-19 ምክንያት ለጋዜጠኞቹ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብልና የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ለማቅረብ መቸገሩን አስታውቋል፡፡

ነፍስ አድን መረጃዎችን በየአካባቢያቸው ቋንቋ የሚስተላልፉት የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃንም ሚዲያ እንደ ልብ ለማግኘት ዕድል ለሌላቸው አናሳና የተገለሉ ማህበረሰቦች ለማድረስ ተመሳሳይ የፋይንስ ችግር ስላጋረጠማቸው ህልውናቸው አስጊ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ኢንዱስትሪው ገቢው በከፍተኛ መጠን በመቀነሱ የስራ ማስኬጃ የገንዘብ እጥረት ችግር ላይ ወድቋል፡፡ አንድ የመገናኛ ብዙሃን ሀላፊ ሁኔታውን ‹ ሚዲያዎቻችን ያጋጠማቸው የገንዘብ እጥረት የኮረና ወረርሽ ህመምተኞች ኦክስጅን ሲያጥራቸው ለመተንፈስ እንድሚቸገሩት ነው” ሲሉ ገልጸውታል።  ባለፈው ሚያዝያ ወር ብቻ አንድ የህትመት መገናኛ ብዙሃን ስራውን ለማቆም ሲገደድ ሌላ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞቹን ሰብስቦ ደሞዝ መክፈል እንዳልቻለ ከገለፀላቸው በኋላ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከስርጭት ውጭ ሆኗል፡፡ ሌሎች መገናኛ ብዙሃንም ተመሳሳይ ስጋታቸውን እየገለፁ ነው፡፡

ቀደም ባሉት ወራትም የቢራ ምርቶች ማስታወቂያ በብሮድካስት መገናኛ ብዙሃን ላይ እንዳይተላለፉ በመደረጉ ሳቢያ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እስከ 40 ከመቶ የሚሆነውን ገቢያቸውን አጥተዋል፡፡ የሀብት ኢንቨስትመት በሚዲያ ዘርፉ አናሳ መሆን፣ በቀደመው አስተዳድር የዘርፉን እድገት ያቀጨጩ ሕጋዊና አስተዳድራዊ ማነቆዎችን ለማሻሻል የተያዘው ጥረት ከመጓተቱ ጋር ተዳምሮ የኮቪድ-19 ጫና ለዘርፉ ሕልውና ከባድ የሕልውና ስጋት ጋርጧል።

የመገናኛ ብዘዙሃኑ ተዋንያን ይህንን ችግር ለማስወገድ የኢትዮጵያ ሲቪክ መረጃ ጥምረት / the Ethiopian Civic Information Consortium / የተሰኘ የበጎ ፈቃደኛ ቡድን በማቋቋም በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ላይ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እያደረሰ ያለውን ተጽእኖ ለማስወገድና የህዝብ ፍላጎትን መሰረት አድርገው የሚሰሩ ጋዜጠኞችን ለመታደግ ለዚህ የፈተና ጊዜ ከዚህ በፊት ያልነበረ መፍትሔ ለማፈላለግ የተለያዩ ስልቶችን ቀይሰዋል፡፡ ጥምረቱ ተቋማዊ ቅርጽ እስኪኖረው ድረስ ጊዚያዊ ተቋማዊና አስተዳደራዊ ቤቱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤትን አድርጎ፤ በራስ ገዝ ቁመና ስራውን እያከናወነ ይቆያል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ዘርፉን ወክሎ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚደረጉ ግንኙንችቶችን የሚያስተባብርና እንዲመራ ከስምምነት ተደርሷል።

COVID-19 የመገናኛ ብዙሃን ደራሽ ድጋፍ መስጠት ለምን አስፈለገ?

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭት በማህበረሰቡና በመንግስትና በህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ መሠረተ ልማት ላይ ያልተለመዱ ችግሮችን ጋርጧል። ኮቪድ-19ኝን በተመለከቱ ወቅታዊ፤ተገቢና ተአማኒ የህይወት አድን ዘገባዎችን ለማህበረሰቡ ለሚያቀርቡ ወሳኝ የፊት መስመር ተፋላሚዎች መሆናቸው የሚታመነው የመገናኛ ብዙሃንና ጋዜጠኞችም ሕልውናቸው በፈተና ላይ ወድቋል።

በድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና ችግሮች ወቅት መንግስትን ጨምሮ የተለያዩ ዘርፎች በመተባበር ፈጣን የመገናኛ ብዙሀንና ጋዜጠኞች አቅም ግንባታ ስራ ማከናወን ይገባቸዋል።

ኮረና ቫይረስ ለህዝብ ፍላጎት የቆመ ጋዜጠኝነት ላይም ሌላ ፈተና ይዞ መጥቷል፡፡ ይህም የማስታወቂያ ገቢ መቀነስ በጋዜጠኞች ደህነነት ላይ ያልተለመደ ስጋት አስከትሏል፡፡ መገናኛ ብዙሃን እስከ 60 ከመቶ የሚሆነውን ገቢያቸውን ከማስታወቂያ ለመሰብሰብ አለመቻላቸውና አሁንም ገቢያቸው በፍጥነት ማሽቆልቆሉን በመቀጠሉ፤ ለጋዜጠኞችና ለድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቻቸው ደሞዝ ለመክፈል አለመቻልና የስራ ማስኬጃ ገንዘብ እጥረት እንዲጋጥማቸው አድርጓል፡፡ ወረርሽኙን ለመዋጋር ከሚዲያ ተቋማትና ሰራተኞቻቸው የሚገኘው መረጃ በማሕበረሰቡ ዘንድ የሚፈጥረው ግንዛቤ ከኮቪድ-19 ጋር ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት ወሳኝ የስኬት ከመሆኑ ጋር ተዳምሮ ጉዳዩን አሳሳቢ አድርጎታል።

 1. ግብና ዓላማዎች

የዚህ መርሃግብር ስልታዊ ግብ ኮቪድ-19ኝ በተመለከተ የሚተላለፉ የማኅበረስብ ግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶችን (PSAs) የግብር ከፋዮችን ገንዘብ ወጭ በማድረግ ወይንም ወጭን መጋራት፣ የጋዜጠኞችን ደሞዝና የስራ ቅጥር በመከላከል የሚዲያ ስራን ማስቀጠል፣ እንዲሁም ለሚዲያ ተቋማት የፋይናንስ እፎይታና የዝቅተኛ ወለድ ብድሮን እንደ መሳሪያ መጠቀምን ማበረታታት ነው፡፡

ዓላማዎች

 • ወቅታዊና ህይወት አድን የሚባሉ የህዝብ አግልግሎት ማስታወቂያዎችንና ሌሎች የኮረና ቫይረስ ትምህርቶችን በብዛት በማዘጋጀት ለህዝብ ማሰራጨት። በተለይም የማስታወቂያ ገቢ ላጡ ሚዲያዎች የግብር ከፋዩን ገንዘብ በመጠቀም የህዝብ አግልግሎት ማስታወቂያዎችን በህትመት፤ በብሮድካስትና በዲጂታል መገናኛ ብዙሃን ማስነገር ፤
 • በ2009 ዓ.ም ገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት መ/ቤቶች ማስታወቂያዎችን በንግድ መገናኛ ብዙሃን እንዳያስነግሩ የማያበረታታውን መመሪያ ማሻሻል ወይም ማገድ። ይህም ሁሉም የፌደራል መስሪያ ቤቶች ማስታወቂያዎቻቸውን ባሉት የመገናኛ ብዙሃን በሚዛናዊነትና በግልፅነት እንዲያስነግሩ ያግዛቸዋል፤
 • መገናኛ ብዙሃን ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ የህይወት አድን መረጃን ለህብረተሰቡ የሚያሰራጩት መረጃ የማስታወቂያ ገቢን መሠረት በማድረግ በመሆኑ፤ በአሁኑ ወቅት ይህ ገቢ በመቀነሱ ሳቢያ የመረጃ ስርጭቱ እንዳይስተጓጎልና የመረጃ ፍሰቱ እንዲቀጥል የደረሰባቸውን የገንዘብ እጥረት እንዲቋቋሙ ማገዝ፤
 • በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ ሰራተኞች የሚከፈለውን የደሞዝ ገቢ ግብርንና የጡረታ መዋጮን ለአምስት ወራት ያለ ቅጣትና ያለ ወለድ እንዲጠቀሙበት ማድረግ፤ በዚህ የደሞዝ ገቢ ግብር ማበረታቻ የግብር ከፋዩን ገንዘብ የሚወስዱ የሚዲያ ተቋማት በገንዘብ እጦት ሳቢያ ሠራተኞቻቸውን እንዳይበትኑ ግዴታ ይጥልባቸዋል፤
 • የሚዲያ ተቋማት እየተጋፈጡ ያሉትን የደሞዝና የስራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመቋቋም የአነስተኛ ወለድ ብድር ዋስትና መስጠት፤
 • የመገናኛ ብዙሀን ድርጅቶች የበሽታው ወረርሽን እስከሚቆይበት ጊዜ ድረስ የሚዲያ ስራ እንዳይቋረጥ በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በኩል የስርጭት አገልግሎት ክፍያ ምሕረት እንዲደረግ። እንዲሁም የህትመት መገናኛ ብዙህን በተመለከተ በመንግስታዊው ማተሚያ ቤት ብርሃንንና ሰላም ማተሚያ ቤት የዱቤ ህትመት ጊዜ እፎይታ እንዲሰጥ ማድረግ።
 • የፕሮጀክቱ ዘዴዎችና እቅድ

ይህ ፕሮጀክት የኮረና ቫይረስ ወረርሽን በሚቆይበት ጊዜ የሚዲያ ንግድ ስራን ለማቆየት የግብር ከፋዩን ህዝብ ገንዘብ በተገቢ መንገድ ከመንግስት ጋር በትብብር ለመጠቀም የተነደፈ ነው። የሚከተሉት ስልቶችና የትግበራ እቅዶች ዓላማዎቹን ለማሳካት አማራጭ ሆነው ቀርበዋል፤

 ስትራቴጂ /ስልት/ 1- የህዝብ አግልግሎት ማስታወቂያን በግብር ከፋዮች ገንዘብ ክፍያ መደጎም 

ስለ ኮቪድ 19 ህዝብን ለማስተማርና ለማሳወቅ የግብር ከፋዮችን ገንዘብ ለህዝብ አግልግሎት ማስታወቂያ ክፍያ መጠቀም።  መንግስት ለዚህ አግልግሎት የሚውል ገንዘብ መመደብ ወይም ለህዝብ አግልግሎት ማስታወቂያ በጀት ካላቸው ድርጅቶች ወይም እንደ ጤና ሚኒስቴር ካሉ የመንግስት አካላት መሰብሰብ።

የማሳመኛ ምክንያቶች

የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ለህዝብ መረጃን በማዘጋጀትና በማሰራጨት የበኩላቸውን ድርሻ በማበርከት ላይ ይገኛሉ። የህዝብ አግልግሎት ማስታወቂያዎችን በራሳቸው ወጭ ለታዳሚዎቻቸውና አንባቢዎቻቸው ሲያደርሱ ቆይተዋል። ከኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ማህበር የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ ከኮቪድ 19 ጋር የተዛመዱ መረጃዎችንና ልዩ ልዩ ይዘቶችን አዘጋጅቶ ለአድማጭና ተመልካች ለማቅረብ 156 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የአየር ሰዓት አውለዋል፤  መገናኛ ብዙሃኑ  ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን ሲወጡ ከክፍያ ነፃ ህዝባዊ አገልግሎቶችን ያከናውናሉ፤  ምንም እንኳን የህዝብ አግልግሎት ማስታወቂያዎች ትርፍ ነክ ላልሆኑ ተቋማትና ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን የተሰጠ አግልግሎት ተደርጎ ቢወሰድም የንግድ መገናኛ ብዙሃኑም ይህንን አግልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ይህም ከስራው ጋር የተዛመዱ ወጪዎችና የፈጠራ ስራ ወጪዎች የማስታወቂያ የአየር ሰአት ምደባን ያካትታል። በዓለም አቀፍ ወረርሽን ወቅት የዚህ አይነት ማህበራዊ ሀላፊነቶችን መተው ከባድ ይሆናል፤  ሆኖም በዚህ ወረርሽን ወቅት የሚዲያው ኢንዱስትሪ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት እንደ ኦክስጂን የፋይናንስ ገቢ ማግኘት  ይኖርበታል።

ዓላማዎች

ይህንን ዓላማ ለማሳካት ሦስት ዋና ዋና ስልቶች ተለይተዋል፦

 1.  መገናኛ ብዙሃን ስለ ኮቪድ-19 ህብረተሰቡን የማስተማርና የማሳወቅ ተግባራቸውን እንዲወጡ ማበረታታት። ይህ ጥረት የወረርሽኙን ስርጭት ለመከላከል ወሳኝ ነው፤ ለመገናኛ ብዙሃን የክፍያ ማነቃቂያና የህዝብ አግልግሎት ማስታወቂያ ከመንግስት ማግኘታቸው ስለኮቪድ-19 የተሟላና የተረጋገጡ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ለማድረስ ያስችላቸዋል፤
 2. የህዝብ አግልግሎት ማስታወቂያዎ ስርጭት ጋር የተያያዙ ወጪዎችን መጋራት፤ ይህንን ማድረግ መገናኛ ብዙሃን ከማስታወቂያ ያጡትን ገቢ በዚህ መንገድ እንዲያገኙና እንዲያገግሙ ያግዛቸዋል፤
 3. ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዙ የህዝብ አግሎግሎት ማስታወቂያዎችን በህትመትና በብሮድካስት መገናኛ ብዙሃን በማሰራጨት አማራጮችን ማስፋት፤ እንደዚህ ያሉ የማሰራጫ መንገዶች መስፋት መልዕክቶች ወደ ተጠቃሚው ህብረተሰብ በተለያዩ አማራጮች የመገናኛ ብዙሃን እንዲደርሱ ያደርጋል።

የአተገባበር መንገዶች

የዚህን ስልት ግቦች በስኬት ለመተግበር የሚከተሉት ሃሳቦች እንደ አፈፃፀም አማራጮች ቀርበዋል፦

 • ስለ ኮቪድ 19 የሚመለከቱ የህዝብ አግሎግሎት ማስታወቂያዎችን ለማዘጋጀትና ለማሰራጨት የሚውል አዲስ የህዝብ የገንዘብ ቋት መመደብ፤
 • በጤና ሚኒስቴርና ሌሎች አጋር የፌደራል መ/ቤቶች ለኮቪድ 19 መከላከል ከመደቡት የኮሚዩኒኬሽን በጀት ላይ የተወሰነውን ለህዝብ አግልግሎት ማስታወቂያ ዝግጅትና ስርጭት እንዲውል መመደብ፤
 • የኮቪድ 19ን የተመለከቱ የህዝብ አግልግሎት ማስታወቂያ በራሳቸው ተነሳሽነት ፕሮግራም/ዘገባ ለሚያዘጋጁ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ስፖንሰር የሚያገኙበትን አሰራርን መዘርጋት።

ስትራቴጂ/ስልት/ 2 ዝቅተኛ ወለድ ብድርን ያማከለ የፋይናንስ ድጋፍ

በዚህ የችግር ወቅት የሚዲያ ተቋማት ከሚያጋጥሟቸው በርካታ ተግዳሮቶች መሀከል ዋነኛው የእለት-ተእለት ወጪን አሸፋፈን ጉዳይ ነው፤ ከእነዚህ ወጪዎች መሀከል የሠራተኛ ደሞዝ ክፍያዎች፤ የቢሮ ኪራይ፤ የሳተላይት ኪራይና የፍቃድ ክፍያዎች፤ የህትመት ወጪ፤ የኢንተርኔት ወጪና የብድር ክፍያዎች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የመገናኛ ብዙሃን ኢንዱስትሪው በመጪዎቹ ወራቶች ችግሮቹን ለመቋቋምና ሠራተኞቹን ሳይበትን ለመቀጠል እንዲችል ዘርፍ-ተኮር የአለት-ተእለት ወጪዎችን ለመሸፈን የሚያስችሉ የብድር ፋይናንስ ድጋፍ ስልቶችን ማፈላለግ የግድ ነው፡፡

የአጭር ጊዜ፤ ስራ ማስኬጃ የባንክ ብድሮች ለኢንዱስትሪው በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ወሳኝ ነገሮች መሀከል አንዱ ነው፡፡ በመንግስት ዋስትና የተደገፈ የብድር አቅርቦት ሚዲያው ባልተለመደ ሁኔታ ያጋጠመውን የፋይናንስ ችግርና ኪሳራ ለመወጣት ወሳኝ ነው፡፡ በዚህ ረገድ በመንግስት የብድር ዋስትና የሚደገፍ አንደ ኦቨርድራፍት/ Overdraft Facilities/ አይነት ከባንክ የሚገኝን የስራ ማስኬጃ ብድር የተቋማቱን ህይወት ሊታደግ ይችላል፡፡

ሆኖም በአሁኑ ወቅት በገበያ ላይ ያሉት የአጭር ጊዜ የብድር አቅርቦት መንገዶች ከፍተኛ ወለድ የሚጠየቅባቸውና ቋሚ የብድር መያዥያ (ንብረት) የሚፈልጉ በመሆኑ የሚዲያ ኩባንያዎችን የሚያበረታቱ አይደለም፡፡ ስለዚህ ባንኮች የአጭር ጊዜ ብድሮችን በአነስተኛ ወለድ ለሚዲያዎች እንዲያቀርቡ መንግስት ዋስትናና ልሎች ማበረታቺያዎችን ቢያደርግ የሚዲያ ተቋማት ከፍተኛ እፎይታን ሊያግኙ ይችላሉ፡፡

የማሳመኛ ምክንያቶች

ጠንካራ ይዘት ያለው ዜና ውድ ነው፤በተለይም በወረርሽኝ ወቅት ተአማኒና ትክክለኛ የዜና ዘገባ ማግኘት የሞት ሽረት ጉዳይ ነው፡፡ መረጃን ከማዘጋጀትና ከማሰራጨት ጋር የተያያዙ ወጪዎች እየጨመሩ ቢሆንም ገቢ ግን እየቀነሰ ነው፤ በመሆኑም አንዲህ አይነት ያልተለመዱ ተግዳሮቶች ወጣ ያሉ ና ያለተለመዱ ትብብሮችን ይሻሉ፡፡

እንደ እውነቱ ከሆነ ብዙዎቹ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የቢሮ ኪራያቸውንና ሌሎች ወጪዎቻቸውን ለመሸፈን በሚያስችል ቁመና ላይ አይደሉም፡፡ ሌሎች አነስተኛ የሚመስሉ ወጪዎችም ዓመቱን ሙሉ የሚዲያ ኩባኒያዎችን ስራ ማስኬጃ ካፒታል የሚሸረሽሩ ናቸው፡፡

የብሮድካስት ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን እንደ ምሳሌ ብንወስድ አመታዊ 2,507,749.2 ዶላር የሳተላይት አገልግሎት ክፍያ በውጭ ምንዛሬ ይከፍላሉ[2]፤ ምንም እንኳን የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ በራሱ ትልቅ ተግዳሮት ቢሆንም የሚፈለገውን ክፍያ በብር ለመክፈልም ለተቋማቱ አስቸጋሪ እየሆነ መትዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በሀገር ውስጥ ያሉ የራዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የስርጭት ፈቃድ ክፍያ በተቆጣጣሪው መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በኩል  በየዓመቱ ከ 2000 እስከ 5 ሚሊዮን ብር የሚሰበሰብ ሲሆን ይህም ለዓለም አቀፉ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ህብረት/ International Telecommunication Union (ITU) /የሚከፈል ነው፡፡

ከህትመት ሚዲያው አንፃር የፕሬስ የህትመት ዋጋ በአስገራሚ ፍጥነት አያደገ ይገኛል፡፡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመንግስት ይዞታ ስር ያሉት ማተሚያ ቤቶች የፕሬስ ውጤቶች ላይ ተደጋጋሚ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ ሲሆን እስከ 45 ከመቶ የሚደርስ የህትመት ዋጋ ጭማሪ አድርገዋል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት የፕሬስ አሳታሚ ድርጅቶች በህትመት ስራው ዋጋ መናር ሳቢያ ካፒታላቸውን እየበሉ ከመሆኑም በላይ የህትመት ውጤት ሽያጫቸውን በኪሳራ ለማድረግ ተገደዋል፡፡

በሀገራችን የመገናኛ ብዙሃን ገበያ ላይ ሌላው ተግዳሮት ከኮቪድ-19 ወረርሽን ጋር በተያያዘ ለሠራተኞች የደህንነት ማስጠበቂያ ቁሳቁሶችን መግዢያ ተጨማሪ ወጪ ማስፈለጉ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የንግድ እንቅስቀሴው መቀዛቀዙ የአገሪቱ የማስታዊቂያ ገበያ ማሽቆልቆል አምጥቷል፤ ይህም የመገናኛ ብዙሃን ኩባንያዎች ሊቋቋሙት የማይችሉት ፋይናንስ ችግር ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ የማስታወቂያ ገቢ ኮቪድ-19 ከተከሰተ በኋላ እስከ 60 በመቶ ና ከዚያ በላይ አሽቆልቁሏል፡፡

አንደሚታወቀው በንግድ ተቓማት ላይ የከፋ ችግር ሲያንዣብብ የመጀመሪያው ምልክት ስራ ማስኬጃ ካፒታል እጥረት ነው፡፡ስለዚህ መገናኛ ብዙሃን ኮቪድ-19ን በመከላከሉ ዘመቻ ላይ ፊት አውራሪ በመሆን ገንቢ አስተዋፅኦቸውን ለህብረተሰቡ ለማበርከት ቀርቶ ወጪያቸውን መሸፈን እያቃታቸው በመሆኑ የህልውና ስጋት ላይ ይገኛሉ፤

በመሆኑም ይህንን የዝቅተኛ የወለድ  ብድር አቅርቦት ለሚዲያ ኩባንያዎች ማመቻቸት ችግሩን ለመመከት ያስችላል፡፡

ዓላማዎች

 • ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የአጭር ጊዜ የአነስተኛ ወለድ ያላቸው ብድሮችንና የስራ ማስኬጃ ፋይናንስ የሚቀርቡበት መንገዶችን ማመቻቸት፤ ይህም ሲባል የመንግስት ባንክ በሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል ለአነስተኛና መካካለኛ ኢንተርፕራዞች የተፈቀደው የብድር መመሪያ ሚዲያውንም እንዲያካትት በማድረግ ማበረታተት፤
 • የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ክብርና ነፃነታቸውን አስጠብቀው እንዲሰሩ የተለየ ፍላጎት ካላቸው አካላት የሚደርስባቸውን ጫና ለመቋቋም የገንዘብ ስጦታ ከመስጠት ይልቅ ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ፤
 • የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ለሠራተኞቻቸው ደመወዝ የሚከፍሉበትን መንገድ በማመቻቸት የሚዲያ ስራው እንዳይቋረጥ ማገዝ፤
 • ለግማሽ ዓመቱ የገቢ ግብር እፎይታን መስጠት፤
 • የፋይናንስ ተቋማት ለሚዲያ ኩባንያዎች የአነስተኛ ወለድ ብድር የሚሰጡበትን መንገድ ማበረታታ፤

የአተገባበር መንገዶች

አብዛኛዎቹ የሀገራችን መገናኛ ብዙሃን ብድር ለማግኘት የሚያስችለውን የተለመደ መስፈርት ለማማላት አቅማቸው ደካማ ነው፡፡ ከነዚህ መስፈርቶች መሀከል በይበልጥ ሚዲያውን የሚያገሉት ከፍተኛ የብድር መያዢያ ና የወለድ ምጣኔ መሆናቸው ግልፅ ነው፡፡ በዚህ የተነሳ የኮረና ቫይረስ ስርጭትን በተመለከተ ሃላፊነታቸው እንዲወጡ ለማድረግ መንግስት በአነስተኛ ወለድ ብድር ኩባንያዎቹ የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት፤

ስትራቴጂ/ ስልት/ 3 የሠራተኞች ደመወዝ ዋስትና ፕሮግራም

ይህ የሰራተኞች የደመወዝ ዋስትና ፕሮግራም መገናኛ ብዙሃን በኮቪድ-19 ወቅት ለህብረተሰቡ ማስተላለፍ ያለባቸውን ትክክለኛ መረጃ እንዳያቋርጡ የሚያግዝ ሲሆን ከወረርሽኙ ጋር ነተያያዘ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ላይ የተጋረጠውን የስራ ዋስትና ስጋት ያስወግዳል።

የሚዲያ ተቋማት ለመጪዎቹ አምስት ወራት ከሰራተኞች ደሞዝ ላይ የሚቆርጡትን የስራ ገቢ ግብርና የጡረታ መዋጮ እንዲጠቀሙበት ቢደረግ በቀጣይነት በጋዜጠኞችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ላይ የሚኖረውን የስራ እጦት ዋስትና ችግር ይቀርፋል። በዚህ ረገድ የክትማ አስተዳደር ና የፌደራል አካላት የጀመሩት ጥረት ቢኖርም አሁንም መንግስት ጅምሮቹን ወደ ስራ በማስግባትም ሆነ ሚዲያው ተጠቃሚ አነዲሆን ማድርግ ቢችል ትልቅ ድጋፍ ነው፡፡

መንግስት በዚህ በኩል የሚወስደው እርምጃ የሚዲያ ኩባንያዎቹ በወረርሽኙ ሳቢያ ያጋጠማቸውን የገንዘብ እጦት እንዲሻገሩና ሠራተኞቻቸውን እንዳያሰናብቱ ያስችላቸዋል፡፡

ስትራቴጂ/ስልት/ 4 የግብር እፎይታ ፕሮግራም

ይህ የግብር እፎይታ ፕሮግራም በየወሩ ኩባንያዎቹ ከቫትና ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ ለመንግስት የሚከፈለውን ገንዘብ ለመጪዎቹ አምስት ወራት እንዲጠቀሙበት ማድረግ ጤናማ የገንዘብ ፍሰት እንዲኖር ያግዛል።

የማሳመኛ ምክንያቶች

መገናኛ ብዙሃን ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ አስፈላጊ መሳሪያ በመሆናቸው ጠያቂ ህብረተሰብ በመፍጠር ሂደት ና ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው ስርአት እንዲፈጠር ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡ መገናኛ ዙሃኑ ይህንን የተለየ ሚና እንዲወጡ የሰው ሀይላቸውን ማሰልጠን ይጠበቅባቸዋል፡፡ በአንደዚህ መሰል ድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና ችግር ና የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ በሚያጋጥምበት ወቅት የሚዲያ ባለሙያን ማጣት ችግሩን ይበልጥ ሊያባብሰው ይችላል፡፡

ዓላማዎች

 • የሚዲያ ኩባንያዎቹ በየወሩ ለመንግስት መክፈል ያለባቸውን የሥራ ገቢ ግብርና ሌሎች ታክሶችን ራሳቸው ጋር እንዲያቆዩ ማድረግ፤
 • ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሰው ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ለመጪዎቹ አምስት ወራት ኩባንያዎቹ ያለ ቅጣትና ወለድ እንዲጠቀሙበት ማድረግ፤
 • የግብር እፎይታ ለኩባያዎቹ መስጠት ከወረርሽኑ ጋር ተያይዞ የሚፈጠርባቸውን የገንዘብ እጥረት ለመቀነስ ከማስቻሉም በላይ ስለ ወረርሽኑ የህይወት አድን የተሟላ መረጃን ለህብረተሰቡ ለማድረስ ያስችላቸዋል፤
 • የሠራተኞች ደሞዝ ክፍያ ፕሮግራም ተግባራዊ መደረግ መገናኛ ብዙሃኑ ለመጪዎቹ አምስት ወራት ያለ ቅጣትና ወለድ በሚያገኙት ገንዘብ ለሠራተኞቻቸው የስራ ዋስትና እንዲሰጡ ያስችላቸዋል፡፡

የአተገባበር መንገዶች

 • የሚዲያ ኩባንያዎቹ በየወሩ ለመንግስት መክፈል ያለባቸውን የሥራ ገቢ ግብርና ሌሎች ታክሶችን ራሳቸው ጋር እንዲያቆዩ ማድረግ፤
 • ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሰው ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ለመጪዎቹ አምስት ወራት ኩባንያዎቹ ያለ ቅጣትና ወለድ እንዲጠቀሙበት ማድረግ፤
 • ምንም እነካን የማስታወቂያ ገበየው መውደቅ በየወሩ ለመንግስት መክፈል ያለባቸውን የሥራ ገቢ ግብርና ሌሎች ታክሶች ላይ የራሱ የሆነ ተፅዕኖ ቢኖርውም ከሌሎች ስልቶች ጋር በጥምረት ሲተገበር ለሚዲያ ኢነዱስትሪው ቀላል የማይባል ማተናፈሻ ሊሆን ይችላል።

ስትራቴጂ/ስልት/- 5   ዓመታዊ የአገልግሎት ክፍያንና የማተሚያ ቤት ክፍያ ማዘግየት

መንግስት ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የሚከፈለውን የብሮድካስት ሚዲያውን ዓመታዊ የአገልግሎት ክፍያ ማዘግየት፤ የህትመት ሚዲያውን በተመለከተ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ጋር በመሆን የህትመት ክፍያውን ለተወሰነ ጊዜ በዱቤ እንዲሆን ቢያደርግ በአሳታሚዎች ላይ የሚኖረውን ጫና ይቀንሳል፤

የማሳመኛ ምክንያቶች

የመገናኛ ብዙሃን ኩባንያዎች በየዓመቱ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የሚከፍሉት ዓመታዊ የአገልግሎት ክፍያ የተለያየ መጠን ያለው ነው፤ ይህም ሁለት ሺ ብር ከሚከፍሉት የማህበረሰብ ራዲዮ ጣቢያዎች ጀምሮ እስከ 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር እስከሚከፍለው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ድረስ ይለያያል፤ ምንም አንኳ ክፍያው በመንግስት ደርጃ ሲታይ አነስተኛ ቢመስሉም ከተቋማቱ አንፃር ግን በዚህ ወሳኝ ሰዓት የሚሰጣቸው እፎይታ ፈፅሞ የማይናቅ ነው፡፡ ለአሳታሚዎች የህትመት ከፍያ አንዱ ከፍተኛ ወጪያቸው ነው፡፡ በመሆኑም የዱቤ ህትመት አግልግሎት የኮቪድ-19 ችግር እስከሚፈታ ድረስ ቢያገኙ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ፡፡

ዓላማዎች

 • በከፍተኛ የካፒታለ እጥረት አየተሰቃዩ ላሉ የሚዲያ ተቋማት የማይናቅ ከስራ ማስኬጃ ወጪያቸውን ያማከለ እፎይታ ጊዜ በመስጠት ከኪሳራ ና መዘጋት መታደግ፤

የአተገባበር መንገዶች

ከኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ማህበር የተሰበሰበው መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ በየዓመቱ ለመንግስት የሚከፈለው የአገልግሎት ፈቃድ ክፍያ 10 ሚሊዮን ብር ይሆናል፡፡ ይህ አሀዝ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አተዳደሮች የሚገኙ የመንግስት የመገናኛ ብዙሃንን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን ወጪ ያካትታል፡፡ እነዚህ የመገናኛ ብዙሃን 7 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እንዲከፍሉ በህግ ይገደዳሉ፤ 75 ከመቶ የሚሆነው ድርሻ የኢቢሲ ብቻ ነው፤

የንግድ ብሮድካስተሮችን በተመለከተ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የአገልግሎት ፈቃድ ክፍያ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የሚከፍሉ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የሚከፍለው ነው፡፡ የማህበረሰብ ራዲዮ ጣቢያዎች በአማካይ በዓመት እስከ 100 ሺ ብር የአግልግሎት ፈቃድ ክፍያ ገቢ ያደርጋሉ፡፡

መንግስት የብሮድካስተሮችን ዓመታዊ የአገልግሎት ፈቃድና የህትመት ክፍያን ቢያራዝም ሚዲያዎቹ በኮቪድ 19 ሳቢያ ያጋጠማቸውን የገቢ እጥረት ጫና ይቀንስላቸዋል፡፡

የመንግስት የብድር ዋስትና  (ያለ መያዥያ የሚሰጥ ብድር) ዝቅተኛ ወለድ የስራ ካፒታል / የስራ አገልግሎት  ብድሮች መስጠት የአጭር ጊዜ የፋይናንስ ጉድለትን  እና የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመሸፈን ይረዳል ከመዘጋት የዳነ ዘላቂ ሚዲያ ፤ ለሠራተኞች ዘላቂ የደመወዝ ዋስትና፤

የተመቻቸ የኮቪድ-19 የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ማስቻል፤

 

በ2009 በገንዘብ ሚኒስቴር የወጣውንና የህዝብ አግልግሎት ማስታወቂያን በንግድ ሚዲያው ላይ እንዳይተዋወቁ የሚከለክለውን መመሪያ ማሻሻል፤ ኮቪድ–19 የተመለከቱ የተለዩ ዘገባዎች/ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት

 

የቀነሰውን የማስታወቂያ ገቢ እንዲያንሰራራ ማድረግ

በመረጃ የበለፀገ ህዝብ ማፍራት

 

የደመወዝ ክፍያ ግብሮችን መያዝ፤

የፊስካል እፎይታ

ቅጣቶች ማንሳት / የወለድ ክፍያዎች ማስቀረት

 

ለአምስት ወራት መዘግየት ፣ የደመወዝ ክፍያ እንዳይቐረጥ ማድረግ፤

የገንዘብ እጥረትን መቅረፍ

 

የስራ ዋስትና ይጠበቃል፤

ጋዜጠኛ ከ ኮቪድ-19  እና ከዛም በኋላ ለህዝብ ማገልገሉን ይቀጥላል፤

 

የስርጭት የአገልግሎት ክፍያዎችን ማስቀረት፤የዱቤ ህትመት ስርአቶችን መዘርጋት

 

ክፍያዎችን ማስቀረት ና የዱቤ ህትመት ስርአቶችን በመዘርጋት የስራ ማስኬጃ  ካፒታል እጥረትን መቅረፍቅ፣

 

የስራ ማስኬጃ  ወጪዎች ይቀንሳሉ፤

ሚዲያ መስራቱን ይቀጥላል

በመገናኛ ብዙሃን የተመቻቸ  የኮቪድ-19 ሽፋን እና የመረጃ ልውውጥ ይኖራል፤

 

ፈራሚ የሚዲያ ባለድርሻ አካላት

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት (አስተባባሪ)

የኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ዘርፍ ማሕበር

የኢትዮጵያ አሳታሚዎች ማህበር

የኢትዮጵያ ሲቪክ ኢንፎርሜሽን ጥምረት የስራ ቡድን

የኢትዮጵያ አርታዒያን ማሕበር

የኢትዮጵያ የማሕበረሰብ የመገናኛ ብዙሃን ማሕበር

መርሳ ሚዲያ ኢንስቲትዩት

ተሰሚነት ያላቸው የሚዲያ ተቋም መሪዎች፣ አዘጋጆችና ጋዜጠኞች

 

[1] ከአንድ የሕትመትና ሌላ የብሮድካስት ሚዲያ የማስታወቂያ ገቢ ምልከታ የተገኘ መረጃ (ከጥር ወር እስከ ሚያዝያ ወርሃዊ ገቢ አሃዝ በስዕል 1እና ሁለት ተካተዋል ምንጭ፦ የአሳታሚዎች ማሕበርና የብሮድካስት ዘርፍ ማህበር )

[2] ከኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ማህበር የተገኘ መረጃ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe