ዜናአምስት የንግድ የቴሊቪዥን ጣቢያዎች የስርጭት ፈቃድ ሊሰጣቸው ነው

አምስት የንግድ የቴሊቪዥን ጣቢያዎች የስርጭት ፈቃድ ሊሰጣቸው ነው

አምስት የንግድ የሳተላይት ቴሌቪዥን ብሮድካስት አገልግሎት ጣቢያዎች ፈቃድ እንዲሰጣቸው መወሰኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን አስታውቋል።
ፈቃዱን የሚያገኙት ጎህ ቴሌቪዥን፣ ኤፕላስ ቲቪ፣ ሸካል ቲቪ፣ ከገበሬው ቴሌቪዥን እና ኢሲኤን ቴሌቪዥን መሆናቸውን ባለስልጣኑ አስታውቋል።
ፈቃድ የሚሰጣቸውም የፋይናንስ አቅምና ምንጫቸው ስራውን ለማስኬድ አስተማማኝ እንደሆነ በመታመኑ ነው ያለው ባለስልጣኑ፣ አገልግሎቱን ለመስጠት ድርጅታዊ ብቃት ያላቸው በመሆኑ እና በፕሮጀክት ሰነዳቸው ያቀረቧቸው መሳሪያዎችና ቴክኖሎጂዎች አገልግሎቱን ለመስጠት ብቃት ያላቸው ስለመሆኑም ተጣርቶ ውሳኔ ላይ መደረሱንም መግለጫው አመልክቷል።
የንግድ ቴሌቪዥን ፈቃድ ለማገኘት የቀረቡ አመልካቾች በባለሥልጣኑ መስሪያ ቤት በመቅረብ ውል እንዲዋዋሉና ከዛሬ ጅምሮ ፈቃዳቸውን መውሰድ እንደሚችሉም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe