ዜናበጋዜጠኞች ላይ ጥቃት ያደረሱ አካላት አለመጠየቃቸው የንግግር ነፃነትን እንደሚጎዳ ዩኔስኮ አስታወቀ፤

በጋዜጠኞች ላይ ጥቃት ያደረሱ አካላት አለመጠየቃቸው የንግግር ነፃነትን እንደሚጎዳ ዩኔስኮ አስታወቀ፤

ዛሬ ዩኔስኮ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጋዜጠኞች ላይ የሚደርስ ጥቃትን ለማስቆምና ተጠያቂነትን ለማምጣት የሚያከብረው ቀን ‹ International Day to End Impunity for Crimes Against Journalists on 2 November.> ዛሬ እየተከበረ ነው፤ ባለፉት ዓመታት በዓለም ዙሪያ በጋዜጠኞች ላይ ጥቃት የፈጸሙ የፀጥታ አካትና ባለስልጣናት የሚጠየቁት ከ10ሩ 6ቱ ነበር፤ አራቱ አይጠየቁም ነበር፤ ዘንድሮ ግን ይሄ ቁጥር ጨምሮ ከ10ሩ ወደ 9 ከፍ ብሏል ፤ የሚጠየቀው አንዱ ብቻ ነው ማለት ነው፤
በ2020/21 ብቻ በመላው ዓለም 117 ጋዜጠኞች የተገደሉ ሲሆን 91 ያህሉ የተገደሉት ከስራ ውጪ ሲንቀሳቀሱ  በመዝናኛ ቦታ፤ በትራንስፖርት ቦታና በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ነው፤ በስራ ላይ የተለያዩ ጥቃቶች የሚደርስባቸው ሴት ጋዜጠኞች ቁጥርም ባለፈው ዓመት ከነበረው ከ6 ከመቶ ወደ 11 ከመቶ ማሻቀቡን ዩኔስኮ ያወጣው መረጃ ያመለክታል፤ሴት ጋዜጠኞች ለዘገባ በወጡባቸው አጋጣሚዎች ብቻ ሳይሆን በስራ ላይ እያሉም በቅርብ አለቆቻቸው ለሚደርስባቸው ወሲባዊ ትንኮሳ ተጠያቂነት አለመኖሩ አሳሳቢ መሆኑ ተመልክቷል፤
ዩኔስኮ በጋዜጠኞች ላይ ጥቃት የሚያደርሱ አካላት በፍርድ አደባባይ አለመቆማቸውን ለማስቀረት  በጋዜጠኞች ደህንነት ላይ ያተኮረ የድርጊት መርሃ ግብር አውጥቶ ለአባል ሀገራት ያሰራጨበትን 10ኛ ዓመት እያከበረ ሲሆን መንግስታት ለተቀበሏቸው ስምምነትቶች ተገዢ እንዲሆኑና ጋዜጠኞችን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እንዲያስቆሙ ጥቃት ፈጻሚዎችንም ለፍርድ እንዲያቀርቡ ጠይቋል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe