የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የማሰልጠኛ ማዕከሉን ወደመካከለኛ ኢንስቲትዩትነት ለማሳደግ እንዲረዳው ከዩኔስኮ እና ከኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንሳል ጋር በመተባበር የትምህርት ካሪኩለም ቀረፃን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱ ይታወቃል፡፤
የዚሁም ፕሮጀክት አንዱ አካል የሆነው እና በዩኔስኮ አመቻችነት የኬኒያው KIMC /Kenya Institute of Mass Communication/ የስለጠና አሰጣጥ ምን እንደሚመስል ለማየት እና ልምድ ለመቅሰም ከኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል ፤ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ፣ ከመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን፣ ፣ ከኢትዮጵያ የሴት ጋዜጠኞች ማህበር እና ከዩኔስኩ የተውጣጡ 7 አባላት ያሉበት ቡድን ከሐምሌ 4 ቀን 2013ዓ.ም እስከ ሐምሌ 9 ቀን 2013ዓ.ም ወደ ኬንያ ናይሮቢ በመጓዝ የልምድ ልውውጥ አካሂዴ ተመልሷል፡፡በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት አቶ ሞላልኝ መለሰ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ናቸው፡፡
ቡድኑ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት ያካሄደባቸው ተቋማት
- KIMC /Kenya Institute of Mass Communication/
- CA / Communication Authority of Kenya/
- MCK/ Media Council of Kenya/
- KBC /Kenya Broadcasting corporation/
1.KIMC /Kenya Institute of Mass Communication/
የቡድኑ መጀመሪያ የጉብኝት እና የስልጠና ቦታ KIMC ሲሆን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ስለ ኢንስቲትዩቱ አሰራር እና የስልጠና ሂደት በሚመለከት ለልኡካን ቡድኑ በስላይድ ጭምር የተደገፈ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በ KIMC የነበረው ቆይታ 3 ቀን ሲሆን በእነዚህ ቀናት ውስጥ የኢንስቲትዩትን አወቃቀር ጨምሮ ስልጠና የሚሰጥባቸው ዘርፎች እና ደረጃዎች በዝርዝር ተብራርተዋል፡፡
ከዚያ ውስጥ ኢንስቲትዩቱ ስልጠና የሚሰጥባቸው ደረጃዎችን በሰርተፊኬት፣ በዲፕሎማ፣ በባችለር ዲግሪ እና በማስተርስ ዲግሪ ስልጠና እንደሚሰጥ ተገልጧል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የገቢ ምንጭ ከመንግስት ከሚመደብ በጀት እና ከውስጥ ገቢ ሲሆን የመንግስት ሚኒስትሮች አባላት በሆኑበት ቦርድ የሚመራ በከፊል የመንግስት ሆነ የማሰልጠኛ ተቋም ነው፡፡
ኢንስቲትዩቱ ስለጠና የሚሰጥባቸው ዘርፎች በብሮድካስት ጆርናሊዝም፣ በህትመት ጋዜጠኝነት፣ በፊልም ስራ እና በብሮድካስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሲሆን የስልጠናው 60 ፐርሰንት የተግባር ስልጠና ሲሆን ለዚህ እንዲረዳውም የማሰልጠኛ ተቋሙ ካሜራ፣ ኤዲቲንግ እና የማሰራጫ እቃዎችን ጨምሮ በግብዓት የተሟላ ሲሆን ቀሪው 40 ፐርሰንት ደግሞ ንድፈ ሃሳብ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ የልዑካን ቡድኑ የስልጠኛ ማእከሉን ተቀዋውሮ እንደጎበኘውም ሰልጣኞች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በተግባር ስለጠና ላይ ተሰማርተው የራሳቸውን ፕሮግራም ሲሰሩ እና ቀረፃ ሲኪናውኑ እንዲሁም የኤዲቲንግ እና የግራፊክስ ስራን ራሳቸውን ችለው ለመስራት ሲጥሩ ተመልክተናል፡፡ በአጠቃላይ ተማሪዎቹ ተመርቀው ወደስራ ሲሰማሩ ጀማሪ ሠራተኛ ሳይሆን በቀጥታ ወደስራ መሰማራት በሚችሉበት ሁኔታ ብቁ ሆነው እንደሚወጡ ለመረዳት የቻልን ሲሆን ኢንስቲትዩቱ ከ MCK ጋር በቅርበት እንደሚሰራ እና MCK ም ከኢንስቲትዩቱ ለሚወጡ ጋዜጠኞች እውቅና እንደሚሰጥ ለመረዳት ችለናል፡፡
- CA / Communication Authority of Kenya/
የልዑካን ቡድኑ ሁለተኛ መዳረሻ የነበረው የኬንያ ኮሚኒኬሽን ባለስልጣን መ/ቤት ሲሆን በዚያም ደማቅ አቀባበል ተደርጎልናል፡፡ CA ሶስት ዘርፎች ያሉት ሲሆን የመጀመሪያው የመገኛኛ ብዙሃን ጉዳይን የሚመለከት ሆኖ ፍቃድ የመስጠት እና የመቆጣጠር ስራ ያከናውናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ተቀብሎ የሚመለከት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የኬንያ ሚዲያ ካውንስል በሚወስነው ውሳኔ ላይ በመመስረት መገናኛ ብዙሃን ላይ እርምጃ እስከመውሰድ የሚደረስ ስልጣን አለው፡፡
ሌላው የባለስልጣኑ ስራ የቴሌኮሚኒኬሽን ስራዎችን መቆጣጠር መሆኑን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ሶስተኛው ዘርፍ የፍሪኪዌንሲ ፍቃድ የሚሰጥ እና የሚቆጣጠር ዘርፍ ነው፡፡
- MCK/ Media Council of Kenya/
የኬንያ ሚዲያ ካውንስል ሶስተኛው በልኡካን ቡድኑ የተጎበኘ ተቋም ሲሆን በዚህም በተመሳሳይ ደማቅ የሆነ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
የኬንያ ሚዲያ ካውንስል ሲጀምር በሚዲያው ኢንዱስትሪ ባለቤትነት የተቋቋመ አካል የነበረ ሲሆን እ.ኤ.አ 2013 በወጣ የኮሚኒኬሽን አክት /communication act 2013/ መሰረት በመንግስት እና በሚዲያው ኢንዱስትሪ ባለቤትነት እንደገና ተዋቅሮ ሰፊ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
የኬንያ ሚዲያ ካውንስል ኤክስኪዊቲቭ ቦርድ ከመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና ከሚዲያ ኢንዱስትሪው በተውጣጡ ሃላፊዎች የሚመራ ነው፡፡
የኬንያ ሚዲያ ካውንስል የበጀት ምንጭ፡-
- ከመንግስት ከሚሰጥ የበጀት ድጋፍ
- ከሚዲያዎች ከሚከፈል የብቃት ማረጋገጫ ክፍያ/ accreditation/ ለምሳሌ ኬቢሲ በአመት 2 ሚሊዮን ሽልንግ ሲከፍል እያንዳንዱ ጋዜጠኛ 300 የኬንያ ሽልንግ ይከፍላል
- ከተለያዩ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የሚገኝ ድጋፍም እንደ የበጀት ምንጭነት ያገለግላል፡፡
በአጠቃላይ የሚዲያ ካውንስሉ አመታዊ በጀት 8 ሚሊዮን ዶላር እንደሚደርስ የተገለፀ ሲሆን በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት የሚዲያ ካውንስል የማህበረሰብ ሬዲዮዎችን በበጀት ጭምር ይደግፍ እንደነበር ተገልፆልናል፡፡
የሚዲያ ካውንስሉ ሁለት ዋነኛ አላማዎችን ይዞ የሚንቀሳቀስ ሲሆን የመጀመሪያው ሚዲያውን የመቆጣጠር ስራ ሲሆን ሌላኛው የሚዲያውን አቅም ለማሳደግ የሚሰራው ስራ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የሚዲያ ካውንስሉ ሰፋፊ የስልጠና ስራዎችን በመላ ሀገሪቱ በተከታታይነት የሚሰጥ ሲሆን የልኡካን ቡድኑ ናይሮቢ በነበረበት ወቅት እንኳን በአንድ ቀን በተለያዩ ከተሞች ከ4 በላይ ስልጠናዎችን ሲሰጥ እንደነበር ለመታዘብ ችለናል፡፡ ሌላው የሚዲያ ካውንስሉ በዲፕሎማ ደረጃ ጋዜጠኞችን እያሰለጠነ መሆኑንም ለመረዳት ችለናል፡፡
የሚዲያ ካውንስ በተለያዩ ጊዚያት የሚዲያ መመሪያዎችን እያሳተመ ለኢንዱስትሪው ተደራሽ ያደርጋል፡፡ሌላው የጋዜጠኞች የስነምግባር መመሪያ ላይ ተከታታይነት ስልጠና እንደሚሰጥ የተገለጸልን ሲሆን ይህ የስነምግባር መመሪያ በየ10 አመቱ እንደሚሻሻል ተገልፆልናል፡፡
ሌላው የኬንያ ሚዲያ ካውንስል የሚታወቅበት ተግባር የብቃት ማረጋገጫ የመስጠጥ ተጋባር /accreditation/ ሲሆን ካውንስሉ ለሚዲያው እና ለጋዜጠኞች የሚሰጠው accreditation በUN ጭምር ተቀባይት ያለው መሆኑ ተገልፆልናል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ የሚዲያ ካውንስሉ የሚዲያ ሞኒተሪንግን ጨምሮ የማማከር፣ የአድቮኬሲ እና የጥናት እና ምርምር ስራዎችን ይሰራል፡፡
የቅሬታ ሰሚ ኮሚሽን /Compliant commission/ ዋነኛው የግልግል ዳኝነት አካል ሲሆን ከማንኛውም በሚዲያው መብቴ ተነክቷል ከሚል አካል የሚቀርብለትን ቅሬታ ተቀብሎ ይመረምራል፤ ያከራክራል፡፡ በመጨረሻም ውሳኔ ይሰጣል፡፡ በኮሚሽኑ ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን ለኬንያ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ የኮሚሽኑ አባላት ለመንግስት የተወሰነ አበል ይከፈላቸዋል፡፡
ቅሬታዎች የሚቀርቡት ለኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሲሆን እንደ ጉዳዩ ክብደት እና ቅለት የኮሚሽኑ አባላት በጋራ ወይም ጉዳዮችን ተከፋፍለው አይተው ውሳኔ ይሰጣሉ፡፡
የአሁኑ የኬንያ ፕሪዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ሳይቀሩ በአንድ ጋዜጣ ላይ ስሜ ጠፍቷል ብለው አመልክተው እና ኮሚሽኑ ጋር በግንባር ቀርበው ተከራክረው እንደነበር እና በወቅቱም ውሳኔ እንዳገኙ ተገልፆልናል፡፡
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል ከኬንያ ሚዲያ ካውንስ ጋር አብሮ ለመስራት እንደሚፈልግ በማረጋገጥ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን በኬንያ ሚዲያ ካውንስል በኩልም በተለይ በአቅም ግንባታ በኩል ለማገዝ ዝግጁ እንደሆኑ ተገልፆልናል፡፡
- KBC /Kenya Broadcasting corporation/
የኬንያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሽን የልኡካን ቡድኑ የመጨረሻው መዳረሻ የነበረ ሲሆን በዚያም የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራአስፈፃሚ ስለኮርፖሬሽኑ አጠቃላይ ሁኔታ ለልኡካን ቡድኑ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የኬንያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን መንግስታዊ የሚዲያ ተቋም ሲሆን የበጀት ምንጩ ከመንግስት እና በራሱ ከማስታወቂያ ከሚሰበስበው ገቢ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል፡፡
በኬንያ የቴሌቪዥን ዲጂታላይዜሽን በስራ ላይ መዋሉንም ተረድተናል፡፡ በቀጣይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በተለያዩ መስኮች አብሮ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት የሁለቱ ተቋማት ኃላፊዎች አረጋግጠዋል፡፡
በአጠቃላይ በኬንያ ሀገር ያደረግነው የልምድ ልውውጥ ጉብኝት ከፍተኛ ልምድ የቀሰምንበት በመሆኑ ጉብኝቱን ላዘጋጀው ሌኔስኮ የከበረ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡