ተወዳጅ ሚዲያ ያዘጋጀውና የሪፖርተር ጋዜጣን የሚያሳትመው ሚዲያ ኤንድ ኮሚዩኒኬሽን ሴንተር (ኤምሲሲ) ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አማረ አረጋዊ ታሪክን የያዘው የድምፅ ዶክመንተሪ መስከረም 13 ቀን 2014 ዓ.ም. ተመርቋል፡፡
የሰማንያ ደቂቃ የጊዜ ፍጆታ ያለውን ዶክመንተሪን ያዘጋጀውና ያቀናበረው የተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ ነው፡፡ ተወዳጅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ለአገር ውለታ የዋሉ ባለሙያዎችን ታሪክ በዲቪዲና በኦድዮ ሲዲ፣ በዩቲዩብና በፌስቡክ፣ በዊኪፒዲያና በመጽሐፍ መልክ የሚያወጣ ድርጅት መሆኑን በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡
ከዚህ ቀደም የ42 ባለውለታዎችን ታሪክ በሲዲ፣ እንዲሁም ካለፈው ሚያዝያ ጀምሮ ጀምሮ አዲስ በጀመረው የአማርኛ ዊኪፒዲያ ፕሮጀክት፣ የ120 ሰዎችን ታሪክ በኦን ላይን ማውጣቱን የተቋሙ ሥራ አስፈጻሚ ገልጿል፡፡ ፎቶዎቹ የሥነ ሥርዓቱን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡
ፎቶ፡ ታምራት ጌታቸው