ዜናበሀገራችን የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ በርካታ ለውጦች የተመዘገበ ቢሆንም አሁንም ዘርፉ አልፎ አልፎ...

በሀገራችን የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ በርካታ ለውጦች የተመዘገበ ቢሆንም አሁንም ዘርፉ አልፎ አልፎ በሚስተዋሉ ተግዳሮቶች ተጠልፎ ይገኛል

በየዓመቱ ሚያዝያ 25 የሚከበረውን የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ በስካይ ላይት ሆቴል  በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት፤ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንና በዩኔስኮ ትብብር በተካሄደው ዝግጅት ላይ የአቶ መሀመድ ኢድሪስ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር   ባደረጉት ንግግር  ‹በሀገራችን የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ በርካታ ለውጦች የተመዘገበ ቢሆንም አሁንም ዘርፉ አልፎ አልፎ በሚስተዋሉ ተግዳሮቶች ተጠልፎ ይገኛል።› ብለዋል፡፡

የተከበሩ ዶክተር ሄኖክ ስዮም የእለቱ የክብር እንግዳ የተከበሩ የአቶ ታገሰ ጫፎ የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ተወካይ

የተከበሩ የዪኔስኮ ተወካይ ዶክተር ዮሞኮ ዮኮዞኪ

የተከበራችሁ የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት አመራሮች እና አባላት

የተከበራችሁ የፌደራል እና የክልል የሚዲያ ከፍተኛ አመራሮች

የተከበራችሁ የኢፌዴሪ የሰብአዊ መብት ፣ እንባ ጠባቂ ፣ ምርጫ ቦርድ አመራሮች ወይም ተወካዮች

የተከበራችሁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተወካዮች

የተከበራችሁ ለኢፌድሪክ ኤቨርት የምርምር ተወካዮች

የተከበራችሁ በሚዲያ ልማት ዘርፍ የተሠማራችሁ ሲቪል ማኀበራት

የተከበራችሁ ጢሪ የተደረገላችሁ እንግዶች የበዓሉ ተሳታፊዎች

በቅድሚያ ለዚህ ለ30 ጊዜ ” መረጃ ለህዝብ ጥቅም ” በሚል መሪ ቃል በመላው አለም በሚከበረው የዓለም አቀፍ የኘሬስ ቀን በዓል ላይ በመካከላችሁ ተገኝቼ መልዕክቴን እንዳስተላልፍ በመጋበዜ በወከልኩት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን መስሪያ ቤት እና በራሴ ስም ከፍተኛ ደስታ የተሰማኝ መሆኑን ለመገልጽ እወዳለሁ።

በመቀጠል ይህ በዓል እንዲህ በተሳካ ሁኔታ እንዲከበር ላስተባበሩ መድረኩን በፋይናንስ እና በልዩ ልዩ አግባቦች ድጋፋቸውን ላበረከቱ ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ፣ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፣ ለዮኔስኮ ኢትዮጵያ ፣ ለኢፌድሪክ ኤቨርት እና ሌሎችም በዝግጅቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፎ ላደረጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ከፍተኛ ምስጋናዬን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ።

የተከበሩ የእለቱ የክብር እንግዳ ፤ የተከበራችሁ የበዓሉ ተሳታፊዎች

እንደሚታወቀው ሀገራችን ባለፉት ሶስት አመታት ከተመዘገብ ለውጦች መካከል የኘሬስ ነጻነትን በማክበር የመገናኛ ብዙሃን በማስፋፋት የተሰራው ስኬትማ ለውጥ ሳይጠቀስ የማይታለፍ የመንግስት እና የመገናኛ ብዙሃኑ የጋራ ክትትል ውጤት ነው። በእነዚህ አመታት በሀገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የዘርፉ ተዋናዮች ማለትም ጋዜጠኞች እና የጋዜጠኞች ማኀበራት ፣ የሚዲያ ባለቤቶች የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ሲያነሳቸው የነበሩ ልዮ ልዮ የመብት ጥያቄዎች እና አስቻይ የኘሬስ ነጻነት ከባባዊ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ላነሳቸው ሀሳቦች ምላሽ በመስጠት ረገድ በርካታ ተግባራት ተከናውኗል። ከነዚህ መካከል በቅርብ ቀን የመገናኛ ብዙሃን ፖሊስ ጸድቆ መውጣቱ ፣ የቀድሞ የብሮድካስት ባለስልጣን አዋጅ የሻረው አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ፣ ባለስልጣኑ ቀደም ሲል ሊያከናውናቸው ከነበሩት የብሮድካስት መገናኛ ብዙሃን ክትትል እና ቁጥጥር በተጨማሪም የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን ለመመዝገብ እና ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ ስልጣን ተሰጥቶት ጸድቆ ስራ ላይ መዋሉ የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ ለመከላከል አዋጅ ወጥቶ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ የሚጠቀስ ናቸው።

ከላይ ከተጠቀሱት የለውጥ ስራዎች በተጨማሪም በሀገራችን ለበርካታ አመታት ሲሰራበት የቆየው የአንድ ወገን ቁጥጥር እና የመገናኛ ብዙሃን ክትትል አግባብ ይልቅ በአዲስ የቁጥጥር ሞዴል ማለትም በትብብር ላይ የተመሠረተ የእርስ በእረስ የቁጥጥር ስርዓት የሚያሳልጡ አሰራሮች መዘርጋት ተችሏል። ይህንን ተከትሎ ከበርካታ አመታት ውጣ ውረድ በኋላ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት እውን ሆኖ ተቋቁሟል። ከምክር ቤቱ መደራጀት በመከተል የኢትዮጵያ አርቲያን ማኀበር ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቶች ማኀበር ፣ የብሮድካስቶች ዘርፍ ማህበር ወዘተ ተደራጅተዋል። በሌላ በኩል አለማችን በአሁኑ ወቅት እየተጋፈጠችው ያለው የመረጃ መዛባት ቀውስ ሀገራችንም ለአደጋ አጋልጣት ይገኛል። በዚህም ከማህበራዊ ሚዲያ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የመረጃ መዛባት ሀሰተኛ አሳሳች መረጃዎችን በሀገር ውስጥ ሆነ በውጭ በተፈጠሩ ኘላትፎርሞች በመጠቀም ተቋማትን፣ ግለሰቦችን ቡድኖችን እንዲሁም ሀገራትን ለከፍተኛ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውስ በማስከተል በራሱ በኘሬስ ነጻነት ላይ ጭምር አዳጋ እየጋበዘ ይገኛል። በመሆኑም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሳሳተ መረጃና የጥላቻ ንግግርን ለመግታት የወጣውን አዋጅ ከሚመለከታቸው ሌሎች አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ጋር በመሆን በመረጃ ላይ ተመስርቶ የመቆጣጠር የመከታተል ብሎም የአቅም ግንባታ ስራዎችን እንዲያከናውን የተሠጠውን ነባር እና አዲስ ተልእኮ በቁርጠኝነት የሚወጣበት ይሆናል።

የተከበሩ የእለቱ የክብር እንግዳ ፤ የተከበራችሁ የበዓሉ ተሳታፊዎች

በሀገራችን የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ በርካታ ለውጦች የተመዘገበ ቢሆንም አሁንም ዘርፉ አልፎ አልፎ በሚስተዋሉ ተግዳሮቶች ተጠልፎ ይገኛል። ከነዚህ መካከል የመገናኛ ብዙሃን ዘርፉን ሌሎች የሀገሪቱ ህጎች አውቆ አክብሮ የመንቀሳቀስ ችግር ፣ የማህበራዊ ኃላፊነት በአግባብ ያለመወጣት ችግር የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ከማስከበር ይልቅ ግጭትን እና ጦርነትን ሁሉን ባማከለለሁ የሁሉንም ድምጽ በሚዛናዊነት ሪፖርት ከማድረግ ይልቅ በጎሳ ፍላጎትና በጠባብ የፖለቲካ ወገኝትነት ተገፍቶ ችግር የማባባስ እና የማቀጣጠል ዝንባሌ አሁንም የሚስተዋሉ ችግሮች ናቸው።

ዘርፉን ከነዚህ እና መሠል ተግዳሮቶች ማላቀቅ ለነገ የማይባል የሁላችንም ርብርብ እና እና ትግል የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። ባለፉት ሶስት አመታት የኘረስ ነጻነት ለማስከበር የመገናኛ ብዙሃን ለማስፋፋት የተደረጉ ሀገራዊ ለውጦች ተከትሎ በተፈጠረ አስቻይ ሁኔታ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ማህበራት በነጻነት ፍላጎታቸው መደራጀታቸው ወደ ተጨበጭ ስራ መግባታቸው መቻላቸው በልዮ ልዮ የትብብር እና የአቅም ግንባታ ዙሪያ እያደገ የመጣውን የመንግስትና የኘሬስ መልካም ግንኙነት በሚቀጥሉት አመታትም ተጠናክሮ ይቀጥላል።

የመገናኛ ብዙሃን ለመደገፍ የታክሲና ቀረጥ የተያያዙ ችግሮች ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ሆኖ ለመፍታት ባለስልጣን የጀመራችውን ጥረቶች ዳር ለመድረስ እንደሚረባረብ በዚሁ አጋጣሚ ቃል ለመግባት እፈልጋለሁ።

የመገናኛ ብዙሃን ድርጅት በበኩላቸው ከጋዜጠኝነት ሙያ ያፈነገጡ ዘንባዎች የሀገር ብሔራዊ ጥቅሞችን በኘሬስ ነጻነት ሽፋን አሳልፎ ከመስጠት የመታቀብ የጥላቻ ንግግሮችና የተሳሳቱ መረጃዎችን ስርጭት የመከላከል የብዙሀነትና ድምጽ አልባ ድምጾች የሚያገኙበት የሚዛናዊነት መርህ የሚስተናግዱበት ህገ መንግስታዊና ሞራላዊ ሀላፊነት ተግባራው ማድረግ በቀጣይ አመት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርባቸዋል።

በመጨረሻም 6ኛው ሀገራዊ ክልላዊ ምርጫ ሠላማዊ ነጻ ፍትሐዊ ዲሞክራሲያዊ ምስጥራዊ ፍኩኩራዊ ያለበት ምርጫ ሆኖ እንዲቀጥል ሁላችንም ርብርብ የሚጠይቅ ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን በተለይም መገናኛ ብዙሃን የምርጫው ሂደት የተሳካ እንዲሆን ሚዛናዊ ከስሜት የጸዳ ትክክለኛ መረጃ በሚቀርብ ከፍተኛ ሀገራዊ ተልዕኮአቸውን ሊወጡ ይገባል በማለት መልዕክቴን ማስተላለፍ እወዳለሁ።

አመሠግናለሁ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe