ዜናምክር ቤቱ ከባለሥልጣኑ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

ምክር ቤቱ ከባለሥልጣኑ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

 የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት  እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የእርስ በርስ ቁጥጥር ስርዓትን ለማጠናከር የሚረዳ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የስምምነቱ ዓላማ ሁለቱ ተቋማት የሀገሪቱን የመገናኛ ብዙኃን አሰራር ለማዘመንና ለማሳደግ እንዲሁም የእርሰ በርስ ቁጥጥር ስርዓትን ማጠናከርና ተግባራዊ ማድረግን በተመለከተ በትብብር ለመስራት ነው።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ስምምነቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል በመርህ ላይ የተመሰረተ ግንኙነትን በመፍጠር ከሙያው ጋር የተያያዙ ስልጠናዎችንና ማንዋሎችን በትብብር ለማዘጋጀት፣ በሀገሪቱ የሚዲያ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ሙያዊ ስነ-ምግባር የተላበሱ፣ ብቁና ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል እንዲሁም ከህዝብና ከተለያዩ አካላት የሚቀርቡ ቅሬታዎችንና መረጃዎችን በመለዋወጥ የእርስ በርስ ቁጥጥር ስርዓቱ እንዲጠናከር ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ በበኩላቸው የእርስ በርስ ቁጥጥር ስርዓቱን በማጠናከር የመገናኛ ብዙኃን ዘርፉን ለማሳደግ ሁለቱ ተቋማት በመደጋገፍ በጋራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡
በስምምነቱ ወቅት የምክር ቤቱ አባል የሆኑ ሚድያዎችን በሚመለከት ለባለሥልጣኑ የሚቀርቡ ጥቆማዎች እና ቅሬታዎች በምክር ቤቱ በኩል ሙያዊ ውሳኔ እንዲያገኙ የሚደረግበት ሁኔታ እንደሚመቻችም ተገልፇል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ከ60 በላይ የመገናኛ ብዙኃንና የሙያ ማህበራትን ያቀፈ ተቋም መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe