ዜናምክር ቤቱ ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን አመራሮች ጋር አብሮ ለመስራት ውይይት አካሄደ

ምክር ቤቱ ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን አመራሮች ጋር አብሮ ለመስራት ውይይት አካሄደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ አካታች ሀገራዊ ምክክሮችን የማካሄድ አላማ ስንቆ እየተንቀሳቀሰ ካለው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ባደረጉት ገለጻ ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካና የሃሳብ ምመሪዎ እንዲሁም የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል መሰረታዊ በሆኑ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ የሃሳብ አለመግባባት የሚታይ መሆኑን መነሻ በማድረግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 1265/14 ተመስርቶ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ገልጸው የጸጥታ ችግር ካለባቸው አንዳንድ አካባቢዎች በስተቀር በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተሳታፊዎች ልየታና የአጀንዳ መቀበል ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡

ሀገራዊ ምክክሩን ውጤታማ ለማድረግ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ሚና ክፍተኛ ነው ያሉት ዋና ኮሚሽነሩ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የሚደረገውን ውይይት ጨምሮ ከታች ያለው ዜጋ ሃሳቡን በነጻነት የሚገልጽበትን መድረኮች ለብዙሃን ተደራሽ ለማደረግ ተቀራርበን በጋራ ልንሰራ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፤

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የስራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ በበኩላቸው ምክር ቤቱ የፕሬስ ነጻነትን ለድርድር ሳያቀርብ በስነ ምግባር የታነጸ ሚዲያ እንዲገነባ የሚታገል መሆኑን ገልጸው ምክር ቤቱ ከ80 በላይ ተቀማትን በማቀፍ የእርስ በእርስ ቁጥጥር ስርአትን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል፤

የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጁ የተሰጡት ስልጣንና ሃላፊነቶች በሀገሪቱ ውስጥ ለዘመናት የተከማቹ ችግሮችን በውይይት ከስረ መሰረቱ ለመፍታት እድል የሚሰጡት እንደሆነ የጠቀሱት አቶ አማረ ኮሚሽኑ ምን እንደሚሰራ ወይም ምን እንደማይሰራ ግልጽ በማድረግ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ተቀራርቦ መስራት ለነገ የማይባል ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ከአጀንዳ ቀረጻና ከተሳታፊዎች ልየታ በሃላ ህዝባዊ ውይይቶችና ምክክሮች ሲካሄዱ መገናኛ ብዙሃን በምን መልኩ ውይይቶቹን ለህዝብ ተደራሽ እንደሚያደርጉ በኮሚሽኑ የተዘጋጁ ስትራቴጂክ እቅዶች ላይ በቀጣይነት ለመወያየትና ምክር ቤቱ የራሱን ግብአት በማከል የጋዜጠኞችን አቅም በስልጠና በማሳደግ በኩል በጋራ ለመስራት ከመግባባት ላይ ደርሰዋል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe