ዜናምክር ቤቱ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ጋዜጠኞችና የሚዲያ አመራሮች ጋር ተከታታይ ስልጠና ለመስጠት...

ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ጋዜጠኞችና የሚዲያ አመራሮች ጋር ተከታታይ ስልጠና ለመስጠት ውይይት አካሄደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በመላ ሃገሪቱ ለሚገኙ ጋዜጠኞችና የሚዲያ አመራሮች ልዩ ልዩ የስልጠና አይነቶችን አዘጋጅቶ ሲሰጥ ቆይቷል።
ይህንኑ መሰረት በማድረግ በምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ታምራት ኃይሉ የተመራ የልዑካን ቡድን ሰሞኑን በመቀሌ ተገኝቶ ውይይት አካሂዷል።
በፕላኔት ሆቴል በተካሄደው የውይይት ፕሮግራም ላይ የትግራይ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ፣የድምፀወያኔ ቴሌቪዥን፣ የትግራይ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስና ሌሎች በግላቸው የሚንቀሳቀሱ ዩቲውበሮች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ ስለ ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት አላማና አደረጃጀት ገለጻ ያደረጉት አቶ ታምራት ከ80 በላይ አባላትን ያቀፈው ምክር ቤቱ በአዋጅ እውቅና ያለውን የእርስ በእርስ የቁጥጥር ስርዓትን ተግባራዊ ከማድረግ ጎን ለጎን የአቅም ግንባታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልፀው የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ተቋማትም የምክር ቤቱ አባል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
በክልሉ ለሚገኙ የመንግስትና የግል ጋዜጠኞችና የሚዲያ አመራሮች ስልጠናዎችን ለመስጠት በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ከሃላፊዎች ጋር ለመነጋገር የምክር ቤቱ አመራሮች መቀሌ ድረስ መምጣታቸው የሚመሰገን መሆኑ በተሳታፊዎቹ የተገለፀ ሲሆን የክልሉ ጋዜጠኞች ባለፉት አራት ዓመታት በነበረው ነባራዊ ችግር ምክንያት ምንም አይነት ስልጠና ባለማግኘታቸው ይህንኑ ከግምት ያስገቡ ግጭት አገናዛቢ ዘገባዎችና ስነልቦናዊ መነቃቃት ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን ለሁሉም የሚዲያ ባለሙያዎች በተከታታይነት እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል። በስልጠናው አይነት ይዘትና የጊዜ ሰሌዳን በተመለከተ ከአመራሮቹ ጋር በመወያየት ለመወሰን ከመግባባት ላይ ተደርሷል።
በመጨረሻም በክልሉ ቆይታችን ለተደረገልን መስተንግዶ እያመሰገንን በተለይም የትግራይ መገናኛ ብዙኃን ዋና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ተሻለ በቀለ ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል አቶ ታምራት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe