ዜናምክር ቤቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የበይነ መረብ ጋዜጠኝነት የሙያ ስነ ምግባር ደንብ ይፋ...

ምክር ቤቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የበይነ መረብ ጋዜጠኝነት የሙያ ስነ ምግባር ደንብ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የበይነ መረብ ጋዜጠኝነት የሚመሩበት የስነ ምግባር ደንብ አዘጋጅቶ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ፤
መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በማዶ ሆቴል በተካሄደው በዚሁ የምክክር መድረክ ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ እንደተናገሩት በኢንተርናሽናል ሚዲያ ሰፖርት ድጋፍ የተዘጋጀው ደንቡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አማራጭ የመረጃ ማሰራጫ ዘዴ ሆኖ በመጣው የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ላይ የሚሰሩ ጋዜጠኞች እንደ መደበኛው መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የሙያውን ስነ ምግባር አክብረው ለህብረተሰቡ መረጃዎችን ማሰራጨት እንዲችሉ  እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል፤ ሁሉም የበይነ መረብ ጋዜጠኞች ሀሰተኛ መረጃዎችንና ከፋፋይ መልዕክቶችን እያስፋፉ ነው ለማለት አይቻልም ያሉት አቶ አማረ ነገር ግን ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የበይነ መረብ ጋዜጠኞች ከስነ ምግባር ደንቡ በተቃራኒ መረጃዎችን በማሰራጨት አብሮ የመኖር እሴትን እየሸረሸሩ በመሆኑ የደንቡ መውጣት ሙያውን ተአማኒ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል፤
Digital media Particpant
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ በበኩላቸው እንደተናገሩት የበይነ መረብ ጋዜጠኞች በአዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሠረት በህጉ አግባብ ተመዝግበው መንቀሳቀስ የሚችሉ ሲሆን ባለስልጣኑ ህጉን አክብረው ለሚሰሩ  የበይነ መረብ ጋዜጠኞች አስፈላጊውን የአቅም ግንባታና ሌሎች ድጋፎችን ያደርጋል ብለዋል፤
Ato Tamerat and Ato Mesret
የምክር ቤቱ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ታምራት ኃይሉ በምክር ቤቱ የተዘጋጀውን የበይነመረብ የጋዜጠኝነት የስነ ምግባር ደንብ ዋና ዋና ነጥቦች ያብራሩ ሲሆን የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ጋዜጠኞች በበይነ መረብ አማካይነት የሚቀርቡ ዜናዎች፤ ኘሮግራሞች፣ ፎቶዎችና ተንቀሳቃሽ ምስሎች፤ አስተያየቶች፤ ወይም ማስታወቂያዎች የሀገሪቱን ህገ- መንግስት፣ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅን፣ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ፣ የማስታወቂያ አዋጁን፣ የሙያ ስነ-ምግባር መመሪያውን፣ ለቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ የወጡ ህግጋትን፣ ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶችና ፕሮቶኮሎችን እንዲሁም ሌሎች የሀገሪቱን ህጎችን ማክበር እንዳለባቸው መገንዘብ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡
በመጨረሻም የምክር ቤቱ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል  አቶ መሠረት አታላይ ስለ ምር ቤቱ አደረጃጀትና አሰራር ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በስነ ምግባር ደንቡና በምክር ቤቱ አደረጃጀት ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe