ወቅታዊ መግለጫማስታወቂያ፡ - ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር  ቤት

ማስታወቂያ፡ – ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር  ቤት

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የእርስ በእርስ ቁጥጥር ስርዓት መድረክ እነሆ እውን ሆነ!

የኢትዮጵያ-መገናኛ-ብዙኃን-ምክር-ቤት-የግልግል-ዳኝነት-አካል
የኢትዮጵያ-መገናኛ-ብዙኃን-ምክር-ቤት አመራሮችና-የግልግል-ዳኝነት-አካል

በቅርቡ በተካሄደው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ በአባላቱ ሙሉ ይሁንታ ያገኘው የምክር ቤቱ የግልግል የዳኝነት አካል  አባል በሆኑ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በገለልተኝነት መመልከት መጀመሩን ያስታውቃል!

የምክር ቤቱ የግልግል ዳኝነት አካል  አባል በሆኑ የሚዲያ ተቋማት ላይ በተላለፉ ዜናዎች፤ ፕሮግራሞችና የማስታወቂያ ስራዎች ዙሪያ ከህዝብ፤ ከመንግስትና ከግለሰቦች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ተቀብሎ የምክር ቤቱ አባላት ባፀደቁት የጋዜጠኝነት የስነ ምግባር ደንብ መሠረት በመመርምር ውሳኔ ይሰጣል!

በመሆኑም በሚዲያዎቹ ዘገባ መብቴ ተነክቷል የሚል ወይም ቅሬታ ያለው ማንኛውም ግለሰብ ወይም ተቋም አቤቱታውን ለምክር ቤቱ የግልግል ዳኝነት ተቋም በአካል በመቅረብ ወይም በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ማመልከት ይችላል!

ኑ! ቅሬታችሁን መገናኛ ብዙሃኑ ራሳቸው ላቋቋሙት የእርስ በእርስ የቁጥጥር መድረክ  በማቅረብ ያለ ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ሚዲያዎችን ያጠናክሩ!

አድራሻ፡- መስቀል አደባባይ ፊንፊኔ ህንጻ 8ኛ ፎቅ

ስልክ ፡- 0118 134464

ኢሜይል ፡[email protected]

ድረ ገፅ ፡-www.ethiopianmediacouncil.org

 

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe