ዜና«ሚዲያዎች የአገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብሩ ዘገባዎች ላይ ማተኮር አለባቸው»

«ሚዲያዎች የአገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብሩ ዘገባዎች ላይ ማተኮር አለባቸው»

አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ሚዲያዎች የአገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብሩ ዘገባዎች ላይ ትኩረት ማድረግ አለባቸው ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት መምህሩ ዶክተር ሙላቱ አለማየሁ አስታወቁ።

ዶክተር ሙላቱ አለማየሁ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች በተደራጀ አካሄድ የአገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብሩ ዘገባዎችን በስፋት መሥራት ይኖርባቸዋል።

ሚዲያዎች እርስ በእርስ በተሳሰረ አካሄድ ጠንካራ ሕብረት ፈጥረው የኢትዮጵያን ጥቅም ሊያስከብሩ ይገባል። በተለይ በኢትዮጵያ ላይ የሚነዙ የሃሰት መረጃዎችን በተደራጀ መንገድ በማጋለጥና በመመከት ረገድ በሰፊው መሥራት አለባቸው ብለዋል።

በዓለም ተጨባጭ ሁኔታ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር መረጃ እንደ ዋነኛው መሣሪያ እያገለገለ ነው ያሉት ዶክተር ሙላቱ፤ ለዚህም ጠንካራ የሆነ የሚዲያ ግንኙነት እንዲሁም ጠንካራ የሆኑ መረጃ አደረጃጀት ያስፈልገናል ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህ ረገድ የሚዲያ ተቋሙ ብቻ ሳይሆን የየተቋማቱ የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችና የኮሙኒኬሽን ተቋማትን በጋራ ተናበው መሥራት ይጠበቅባቸዋል። በጋራ መሥራቱ የሚፈጥረው ጥንካሬ የሕዝብንና የአገርን ጥቅም በአግባቡ ለማስጠበቅ የሚረዳ ነው ብለዋል።

ዕውነታውን ካየነው ግን የኢትዮጵያ ሚዲያ የአገርን ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ ደካማ ነው፤ በተለይም በኢትዮጵያ ላይ የደረሰውን የዓለምን ጫና መቋቋም አልቻለም። ለዚህ ደግሞ አንደኛው ምክንያት መረጃዎችን በአግባቡ አደራጅቶ አለማቅረቡ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የአገርን ጥቅም በአግባቡ ለማስጠበቅ የሚዲያ ማኅበራት፣ የሚዲያ ግንኙነት ትስስር መድረኮች ትልቅ ጠቀሜታ አላቸው። የእራሳቸውን አጀንዳ በመቅረጽና ስትራቴጂ በመንደፍ ያለውን የፕሮፓጋንዳ ጦርነት በመቀልበስ ረገድ የእራሳቸውን ሚና መጫወት ይችላሉ ብለዋል።

አሁን ባለው ሁኔታ ሁሉም ሚዲያው በአንድ ቋት ውስጥ፣ በአንድ እሳቤና ባለቤትነት ውስጥ አይደለም፤ ይሁንና የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስከበር በአንድ ድምጽ ተባብሮ መሥራት የሚቻልበት መንገድ አለ። በህብረት ጠንካራ ማኅበር ፈጥሮ መንቀሳቀስ ቢቻል የበለጠ ተሰሚነታችን ከፍ ይላል ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ማድረግ ከተቻለ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይሆን ነገ ከነገወዲያ በሚመጡ የጤና የልማትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደአገር ተደማጭ መሆን እንደሚቻል አስረድተዋል።

ጋዜጠኛውም ሆነ ሚዲያው የአገርን ጥቅም ለማስከበር የሕዝቡን ፍላጎት አስቀድመው መሥራት ይጠበቅባቸዋልያሉት ዶክተር ሙላቱ፤ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያውያን የሽብር ቡድኖች ሴራ ተቀልብሶ በጦርነቱ አገር አሸናፊ ሆና የምትቀጥልበትን መንገድ ማየት ዋነኛ ፍላጎታቸው ነው። ስለዚህም ሚዲያው ይህን የሕዝብ ፍላጎት የሚያጠናክሩ ሰፊ ዘገባዎችን መሥራት አለበት ብለዋል።

ምንጭEPA

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe