ዜናመንግሥት ሕገመንግሥታዊ ግዴታውን ሊወጣ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ጠየቀ

መንግሥት ሕገመንግሥታዊ ግዴታውን ሊወጣ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ጠየቀ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የአለም አቀፉ የፕረስ ነፃነት ቀን <<ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ለሁሉም ሰብዓዊ መብቶች መሠረት>> በሚል መሪ ቃል አከበረ።

በኢንተርሌግዥሪ ሆቴል ሚያዝያ 25፤2015 በተከበረው በዚህ በዓል ላይ ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ከተከሰቱት ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች በፀጥታ ኃይሎች የተፈፀመውን ያለፍርድ እስር ጨምሮ፣ ህገወጥ ወይም የዘፈቀደ አፈናን የሚያሳዩ እንደሰብዓዊ መብት ኮምሽን አይነት ተቋማት ያወጧቸው ሪፖርቶችን መነሻ በማድረግ ለመነጋገር ቀኑ ዕድል እንደሚሰጥ ተመልክቷል።

press freedom day
መንግሥት ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር የተያያዙ የወንጀል ተግባሮችን ሁሉ የመከላከል፣ የመመርመር እና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት ቢሆንም ተግባራቱ ሁሉ ግን ኀሳብን በነፃ የመግለፅ መብትን በማያጠብና የዜጎችን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ተሳትፎ በማይጎዳ መልኩ ሊሆን ይገባል።
ማናቸውም ሕግን የማስከበር ተግባራትም በሕግ አግባብ ብቻ መመራት ስላለበት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት መሠረት እንዲኖረው መንግሥት ሕገመንግሥታዊ ግዴታውን ሊወጣ እንደሚገባ ከፕሬስ ካውንስል የወጣው መግለጫ ያስረዳል።(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

FOLLOW US

4,545FansLike
4,545FollowersFollow
4,213SubscribersSubscribe